• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት የለገጣፎ ኆኅተ ገነት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ሕንጻ ቤተክርስቲያን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ በተገኙበት ቅዳሴ ቤት በዓል ተከበረ

ግንቦት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ቅዳሴ ቤቱ ሲከበር ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ፤ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ […]

የደብረ ታቦር የዐራቱ ጉባኤ ቤትና ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ።

ግንቦት 15 ቀን 2018 ዓ.ም የደብረ ታቦር ደብረ ልዑላን መድኃኔዓለም የአራቱ ጉባዔያት ምስክር ጉባኤ ቤት እና የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራረሙ። ​ሀገር በቀል ዕውቀትን (Indigenous Knowledge) ከዘመናዊው ሳይንስ ጋር በማቀናጀት ለሀገር ሁለንተናዊ ዕድገት መሠረት የሚጥል ታሪካዊ የሁለትዮሽ (Bilateral) ስምምነት ሰነድ ዛሬ ተፈርሟል። ​የሁለትዮሽ ስምምነቱን የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሰሎሞን አበጋዝ እና የደብረ ታቦር […]

ወነበሩ በቤተ መቅደስ እንዘ ዘልፈ ይባርክዎ ለእግዚአብሔር ” (ዘወትር እግዚአብሔርን እያመሰገኑ በመቅደስ ኖሩ) ሉቃ 24:53

በመልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ (ቆሞስ) የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ይኽ ኃይለ ቃል ከጌታችን ዕርገት በኋላ ደቀ መዛሙርቱ የነበራቸውን መንፈሳዊ ሕይወት የሚገልጽ ነው። ✍️ አምልኮአቸው ቀጣይነት ያለው ነውና ደቀ መዛሙርቱ ጌታ በአካል ከተለያቸው በኋላ ተስፋ በመቁረጥ አልተበተኑም። በቤተ መቅደስ በመገኘት ምስጋናቸውን ቀጥለዋል። ክርስቲያን በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ሆኖ እግዚአብሔርን በማመስገን መጽናት እንዳለበት […]

የመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ጥሪ!

“ታሪክን ለትውልድ የማሻገር ተራው የእኔ ነው” በሚል መርህ እየታደሰ ለሚገኘው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ለቀሪ ሥራዎች ማጠናቀቂያ ኢትዮጵያውያን እንዲተባበሩ ጥሪ ቀረበ። ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ግንቦት ፲፬/፳፻፲፰ ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ እምብርት የሚገኘው ታሪካዊው የመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ከተቆረቆረ 130 ዓመታትን ያስቆጠረ ታሪካዊ ልዩ እና በሥነ ሕንጻ ቅርጹ በልዩ […]

በዓለ ዕርገት

“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።” ዮሐንስ ፫፥፲፫ 💠ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል በዓለ ዕርገት አንዱ ነው። በዓሉ ከትንሣኤ በ፵ኛው ቀን ይከበራል። “ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።” ሐዋርያት ፩፥፫ 💠በዓለ ዕርገት ለሐዋርያት የየሚላክላቸው አጽናኝ […]

የገዳመ ኢየሱስ አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አባቶችን ቡራኬ ተመረቀ

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ግንቦት ፲፪/፳፻፲፰ ዓ/ም የገዳመ ኢየሱስ አዲሱ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በብፁዓን አባቶችን ቡራኬ ተመረቀ። በሥርዐተ ቡራኬ ቤተ ክርስቲያኑ መርሐ ግብር ላይ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፀለዕ አቡነ ናትኤል የቅድስት ሀገረ ኢየሩሳሌም ገዳማት ሊቀ ጳጳስ ፣ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በሰሜን አሜሪካ የኦሀዮና አካቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ […]

“ዘፍልሰተ ሥጋከ ኮነ በግንቦት {የሥጋህ “የዐፅምህ” ፍልሰት በግንቦት ወር ሆነ) ቅ/ያሬድ

በመልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ (ቆሞስ) የዐዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት ዓመታዊ የፍልሰተ ዐፅም በዓል በሰላም አደረሳችሁ! መፍቀሬ ጥበብ ሰሎሞን፦ “የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው” ምሳሌ 10፥7 በማለት በተናገረው አምላካዊ ቃል መሠረት ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት በየዓመቱ ግንቦት 12 ቀን ፍልሰተ ዐፅማቸው የሚከበር መሆኑ ግልጽ ነው። 1. ልደት […]

ቅዱስነቱም ሊቅነቱም በክብር ይታሰብ!

ማኅቶተ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ የቤተ ክርስቲያናችን ማኅቶት፣ የዓደባባይ መገለጫዋ፣ የውስጥ የአገልግሎቷ አብነት፣ ቤተ ክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ከኦሪት እስከ ራእየ ዮሐንስ ያዜመችበት ልሳኗ፣ የሊቃውንት አባት፣ ኢትዮጵያዊ ዕንቁ ነው። ቅዱስ ያሬድ በ505 ዓ/ም የተወለደ ኢትዮጵያዊ አብሪ ኮከብ ሊቀ ነው። ግንቦት 11 በደብረ ሐዊ የተሠወረበትን ቀን ምክንያት በማድረግ በዓሉን በድምቀት ታከብረዋለች። ዛሬ የሚከበረው የቅዱስ ያሬድ ዜማ ምንጩ […]

የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማዕከል ጋር በመተባበር በአፋን ኦሮሞ የሚያገለግሉ 15 ተተኪ መምህራንን አስመረቀ

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ግንቦት ፱/፳፻፲፰ ዓ/ም ዛሬ የተመረቁት ተተኪ መምህራን ለ3 ወራት ግብረ ዲቁና ፣ኪዳን ፣ ሊጦን ፣ መስተበቁዕ ፣ መልክዓ ሥዕል ፣ መልክዓ ቁርባን ፣ መልክዓ ውዳሴ ፣ መልክዓ ማርያም ፣ መልከዓ ኢየሱስ በአፋን ኦሮሞ እንዲሁም ነገረ ሃይማኖት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፣ የስብከት ዘዴ ፣ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ፣ ነገረ ቅዱሳን ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር […]

30 አዲስ አማንያን በኦርቶዶክሳዊት ጥምቀት ከበሩ!

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ግንቦት ፱/፳፻፲፰ ዓ.ም በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ጀሞ ደብረ ብርሃን አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተክርስቲያን 30 አዲስ አማንያን የሥላሴ ልጅነት አግኝተዋል። በብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለአዳዲስ አማንያን የሚከናወነው የቅድስት ቤተክርስቲያን ሥርዓትም ተፈፅሞላቸዋል። በመርሐ ግብሩ መልአከ ሰላም ዓለማየሁ ተፈራ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት