• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አዘጋጅነት ለማኅበረ ካህናቱና ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የሦስት ቀናት ሥልጠና በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ቃለ በረከት ተጠናቀቀ።

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ሰኔ ፳፯/፳፻፲፰ ዓ/ም በደብረ ነጎድጓድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አዘጋጅነት ለማኅበረ ካህናቱና ለወጣቶች ሲሰጥ የቆየው የሦስት ቀናት ሥልጠና በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ቃለ በረከት ተጠናቀቀ። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሚገኙ ጥንታዊያትና ባለታሪኮች አብያተ ክርስቲያናት መካከል የደብረ ነጎድጎድ ቅዱስ ዮሐንስና መካነ ጎልጎታ ቅድስት […]

በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት የአብነት መምህራን በስብከተ ወንጌል አገልግሎት ላይ ድርሻቸውን እንዲወጡ የሚያስችልና በር የሚከፍት የሥልጠና መርሐ ግብር ተካሄደ። ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ

ሰኔ ፳፭/፳፻፲፰ ዓ/ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ስብከተ ወንጌል ክፍል አዘጋጅነት፣ በክፍለ ከተማው ለሚገኙ የአብነት መምህራን፣ የሊቃውንት ጉባኤ አባላትና ሰባክያነ ወንጌል የተዘጋጀ መንፈሳዊ ሥልጠና ተሰጠ። የመርሐ ግብሩ ዋና ዓላማ የአብነት መምህራንና ሊቃውንት ያላቸውን ጥልቅ እውቀት በመጠቀም፣ በስብከተ ወንጌል ዘርፍ ያላቸውን ተሳትፎ የበለጠ ውጤታማ፣ የበቃና የላቀ እንዲያደርጉ ማስቻል መሆኑ ተገልጿል። ረዳት ፕሮፌሰር መምህር ግርማ […]

የምዕራብ ካናዳ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ በግንባታ ላይ የሚገኘው የሆሣዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያንን ጎበኙ። ሰኔ 25 ቀን 2018 ዓ.ም

ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ የምዕራብ ካናዳ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆሣዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን የሕንጻ አሰሪ ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ በግንባታ ላይ የሚገኘውን ዘመን ተሻጋሪዉን የሆሣዕና መንበረ ጵጵስና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያንን ጎብኝተዋል። የቤተክርስቲያኑ የግንባታ ሂደት በብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ለተመራዉ ልዑካን ቡድን በደብሩ አስተዳዳሪ በክቡር መልአከ ኤዶም ቆሞስ አባ ወልደትንሳኤ ባህሩ እንዲሁም በኢንጅነር […]

በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና የዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ ለአስተዳደር ጉባኤው በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፍ እየሠራ ያለውን የተለያዩ የጥናት ሰነዶች አቀረበ፡፡

ሰኔ 24 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ (አይሲቲ) እና ዲጂታል ሽግግር አማካሪ ኮሚቴ በዘመናዊ የዲጂታል ዓለም ውስጥ ቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አገልግሎቷን ተደራሽ ማድረግ የምትችልባቸውንና አስተዳደራዊ አቅሟን ለማሳደግ የሚረዱ ሙያዊ ምክረ ሐሳቦችንና ስልታዊ ጥናቶችን በማቅረብ እንዲሠራ የተቋቋመ ኮሚቴ ነው፡፡ የኮሚቴው ሰብሳቢ ቀሲስ ዮሐንስ ተስፋዬ ለአስተዳደር ጉባኤ ባቀረቡት ጥናት “ቤተክርስቲያን በቴክኖሎጂ የዳበረ […]

የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ደቀ መዛሙርት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት አስመረቀ።

ሰኔ 20 ቀን 2018 ዓ.ም በብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ሣልሳይ የጉራጌ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የተመሠረተው የወልቂጤ ቅዱስ ዜና ማርቆስ መንፈሳዊ ኮሌጅ፣ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት በነገረ መለኮት ትምህርት ዘርፍ ሲያስተምራቸው የነበሩ የሁለተኛ ዙር ደቀ መዛሙርት በዛሬው ዕለት በታላቅ ድምቀት አስመርቋል። የሀገርና የቅድስት ቤተክርስቲያን ተተኪ አገልጋዮችንና ምሁራንን በማፍራት ላይ የሚገኘው የዚህ ኮሌጅ ታሪካዊ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በከፍተኛ መንፈሳዊ […]

ቤተ ክርስቲያናችን የራሷ የሆነ የዳበረ የቀኖና፣ የፍትሕና የአስተዳደር ሥርዓት ያላት በመሆኑ፣ የመንፈሳዊ ፍርድ ቤቷ ሙሉ ዕውቅናና የሕግ ከለላ አግኝቶ ቢደራጅ በርካታ አገራዊ ጥቅሞችን ያስገኛል:: ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ

የቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ፍርድ ቤት እንደገና ለማቋቋም በቀረበው ረቂቅ አዋጅ የውይይት መርሐ ግብር ላይ ያስተላላፉት መክፈቻ መልእክት አስተላላፈዋል። ሙሉ መልእክታቸው እንደሚከተለው ተቀምጧል። ክቡራንና ክቡራት፣ ክቡራት፣ የዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ተሳታፊዎችና ጥሪ የተደረገላችሁ የክብር እንግዶች፤ በመጀመሪያ፣ የሀገራችንን የፍትሕ ሥርዓት መሠረትና የወደፊት አቅጣጫ ለመቃኘት በተዘጋጀው በዚህ ታላቅ መድረክ ላይ፣ በመገኘታችን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ። ኢትዮጵያ ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረና የዳበረ የመንግሥትነት […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በመንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተከናወኑ ያሉ የልማትና የሕንጻ ዕድሳት ሥራዎችን ጎበኙ።

ሰኔ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ​ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ፣የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጋር በመሆን በመንበረ መንግሥት ግቢ ቅዱስ ገብርኤል ገዳም እየተከናወኑ ያሉ ልዩ ልዩ የሕንጻ ዕድሳትና አዳዲስ የግንባታ ሥራዎችን በቦታው ተገኝተው ተመልክተዋል። ​ብፁዕነታቸው በገዳሙ ባደረጉት በዚህ የሥራ ጉብኝት፥ የቤተክርስቲያኑን ጥንታዊና ታሪካዊ ክብር በጠበቀ መልኩ እየተከናወነ ያለውን የዋናውን […]

ቅዱሳን መላእክት

በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትና ሥርዓት መሠረት፥ መላእክት የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫዎች፣ የፈቃዱ ፈጻሚዎችና የሰው ልጆች ረዳቶች ናቸው። መላእክት… ያድናሉ (ይታደጋሉ)፦ መላእክት እግዚአብሔርን በሚፈሩት ዙሪያ ሰፍረው ከመከራ ያድኗቸዋል። “የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” (መዝ. 33፥7) ይለምናሉ / ያማልዳሉ፦ መላእክት ስለ ሰው ልጆች ምሕረትንና ይቅርታን ወደ እግዚአብሔር ይለምናሉ። “የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ የሠራዊት ጌታ […]

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳምን የሕንጻ ቤተክርስቲያን የዕድሳት ሥራ አፈጻጸም ሂደትን ተዘዋውረው ተመለከቱ።

ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ክቡር ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅና የጠቅላይ ቤተክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች በቁልቢ ደብረ ኃይል ቅዱስ ገብርኤል ገዳም የሕንጻ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገነተ ልዑል ቅዱስ ጊዮርጊስ መቃኞ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ ።

ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ሰኔ ፮/፳፻፲፰ ዓ/ም በአዲስ አበባ ሀገረ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፉሪ ሠፈራ አካባቢ ‎በምትክ በተሰጠ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈው ገነተ ልዑል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መቃኞ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል። ይዞታውን ለማግኘት ከሰባት ዓመት በላይ የወሰደው የዚህ አዲስ ቤተክርስቲያን ቡራኬ ‎መርሐ ግብር ላይ መልአከ ምሕረት ቆሞስ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት