ቅዱሳን መላእክት
በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መሠረተ እምነትና ሥርዓት መሠረት፥ መላእክት የእግዚአብሔር የክብሩ መግለጫዎች፣ የፈቃዱ ፈጻሚዎችና የሰው ልጆች ረዳቶች ናቸው።መላእክት…
“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ዙሪያ ይሰፍራል፥ ያድናቸውማል።” (መዝ. 33፥7)
“የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ የሠራዊት ጌታ ሆይ… የምትቆጣቸውን እነዚህን ሰባ ዓመት የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።” (ዘካ. 1፥12)
“እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል።” (ሉቃ. 15፥10)
“እነሆ፥ ኃያላኖቻቸው በሜዳ ይጮኻሉ የሰላምም መልእክተኞች መራራ ልቅሶ ያለቅሳሉ።” (ኢሳ. 33፥7)
“ጌታዬ ግን የእግዚአብሔር መልአክ እንደሚያውቅ በምድር ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ጥበበኛ ነው።” (2ሳሙ. 14፥20)
“ሁሉ ድኅነትን ይወርሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉ መናፍስት አይደሉምን?” (ዕብ1፥14)
ቃል ያደርሳሉ።
“መልአኩም አላቸው፦ እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ የሚሆን ታላቅ ደስታ የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ።
” (ሉቃ. 2፥10)
“ለእግዚአብሔርም ክብር ስላልሰጠ ያን ጊዜ የጌታ መልአክ መታው፥ በትልም ተበልቶ ሞተ።” (ሐዋ. 12፥23)
ልጅ በኃይል እጅግ ይበልጣሉ።
“ኃይለኞችና የበረቱ፥ የቃሉን ድምፅ ሰምታችሁ ትእዛዙን የምታደርጉ መላእክቱ
ሁሉ…”
(መዝ. 102፥20)
“ዳሩ ግን መላእክት በኃይልና በብርታት ከእነርሱ ይልቅ ምንም ቢበልጡ በጌታ ፊት በእነርሱ ላይ የስድብን ፍርድ አያመጡም።”
2ኛ ጴጥሮስ 2፥11
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
በእነዚህ ቅዱሳን መላእክት ክብርና ጥበቃን የሰጠን አምላካችን ስሙ የተመሰገነ ይሁን። የቅዱሳን መላእክት አማላጅነትና ተራዳኢነት አይለየን። አሜን።
እንኳን አደረሳችሁ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልግሎት/Addis Ababa Diocese Media Service
