ማስታወቂያ
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቅያ
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከዚህ በታች በተጠቀሱት ክፍት የሥራ መደቦች ላይ አመልካቾችን አወዳድሮ በቋሚነት ለመቅጠር ይፈልጋል

የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የትምህርት ዘመን ማስጀመሪያ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ በተገኙበት በይፋ አስጀመረ።
የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም ትምህርት ቤት የ፳፻፲፱ ዓ.ም የመማር መስተማር ተግባሩን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርርክ ጠቅላይ ቤተክህነታ ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት መስከረም ፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም በይፋ አስጀመረ። የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም አስተዳዳሪ መጋቤ […]
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ። ምክትል አምባሳደሩ የአዲስ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ለቅዱስ ፓትርያርኩ ገልጸዋል ።
መስከረም ፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ በኢትዮጵያ የጀርመን ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው በማነጋገር ውይይት አድርገዋል። አዲስ አበባ የሚገኘው የጀርመን ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ፈርዲናንድ ፎን ቫሄ መስከረም ፭ ቀን ፳፻፲፱ ዓ.ም ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ እንኳን አደረስዎ ለማለትና እና መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ ነው በጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ የተገኙት፡፡ በዕለቱም […]
ከአሜሪካ የተመለሱ 17 የኢትዮጵያ መንፈሳዊ የብራና መጻሕፍት ለሰባት ተቋማት ተከፋፈሉ።
በመቅደላ ጦርነት የተዘረፈውን ወንጌል ጨረታ ለማስቆም ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ተገልጿል። መስከረም 5 ቀን 2019 ዓ.ም በኢትዮጵያ የቅርስ ባለስልጣን አዳራሽ በተካሄደ ደማቅ ሥነሥርዓት፣ ከአሜሪካ የተመለሱ 17 ውድ የኢትዮጵያ መንፈሳዊ የብራና መጻሕፍት ለሰባት የኢትዮጵያ ተቋማት በስጦታ ተላለፉ። በዚህ ታሪካዊ የርክክብ መርሐ-ግብር ላይ የባለስልጣኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ ከአሜሪካ የመጡ የአጥኝዎች ቡድን አባላት፣ ታዋቂ አርቲስቶችና የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ተገኝተዋል። የኢትዮጵያ […]
በበአታ ለማርያም ገዳም የ2.5 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ቡራኬ ተቀመጠ።
መስከረም ፬/፳፻፲፱ ዓ/ም የአ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያ በበአታ ለማርያም ገዳም የ2.5 ቢሊዮን ብር ፕሮጀክት ግንባታ የመሠረት ድንጋይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ቡራኬ ተቀመጠ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ በተለይም ከ20ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መግቢያ ወዲህ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ካደረጉ ጥንታውያት ገዳማትና የአብነት ትምህርት ቤቶች መካከል በቀዳሚነት ከሚጠቀሱት የዳግማዊ አጼ ምኒልክ መታሰቢያ […]
የ፳፻፲፱ የምሕረት ዓመትን አስመልክቶ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ተከናወነ።
ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ መሻጋገር አስመልክቶ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐ ግብር መልእክት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽሕፈት ቤት ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የመንበረ ፓትርያርክ ምክልት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ፣ […]
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥራ አስኪያጅና የዋና ክፍል ሐላፊዎች ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀበሉ።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽሕፈት ቤት በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት፣ ከሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመሆን እንኳን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ 2019 ዓ/ም በሰላምና በጤና አሸጋገረዎ በማለት ከብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ ለቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና ለራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተቀበሉ። የእንኳን አደረሰዎ መልእክት ለብፁዕነታቸው ያስተላለፉት የልኡካኑ […]
“በአዲሱ ዓመት የአስተዳደር ችግሮችን ሌላ አካል መጥቶ እንዲፈታልን ከመጠበቅ ይልቅ በጋራ ኃላፊነት መፍትሔ ማምጣት የተሻለው አማራጭ ነው”። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ በመልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት ከሀገረ ስብከቱ ዋና ክፍል ኃላፊዎችና ሠራተኞች ጋር በመሆን ለ2019 ዓ.ም. አዲስ ዓመት፣ ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ በሰላም በጤና አደረስዎ በማለት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የአዲስ ዓመት መልካም […]
“በአዲሱ ዘመንም ሕዝቡ የጠማው ሰላም ነው”ቅዱስነታቸው
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች በክቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀብለዋል። ጳጉሜን ፭/፳፻፲፰ ዓ/ም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ ሐላፊዎች በክቡር ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ መሪነት በአዲስ ዓመት ዋዜማ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክን እንኳን አደረሰዎ በማለት ቡራኬ ተቀብለዋል። […]
“ለሁሉም መድኃኒቱ ቀና አእምሮ ነው”
ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ርእሰ ዓውደ ዓመት ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወተስዓቱ ዓመተ ምሕረት፤ በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች […]
ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ አንዳንድ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡
ዳሽን ባንክ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ለሚያገለግሉ ሠራተኞች ለአዲሱ ዓመት መዋያ የሚሆን ሥጦታ አበረከተ፡፡ በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ዳሽን ባንክ በአበረከተው ስጦታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ ክቡር አቶ አየለ ተሾመ የዳሽን ባንክ የስትራቴጂ ምክትል ፕሬዚዳንት እንደተናገሩት “ዳሽን […]