• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ዝክረ ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ

ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለብፁዕ አቡነ ፊልጶስ ሊቀ ጳጳስ (ከ1928 ዓ/ም – 2007 ዓ/ም) ልደት ብፁዕ አቡነ ፊልጶስ የቀድሞው አባ ገብረ ማርያም ፈለቀ ከአባታቸው ከአቶ ፈለቀ ለውጤ ከእናታቸው ከወ/ሮ አያልነሽ ሙሉ በወሎ ክፍለ ሀገር በላስታ ቡግና አውራጃ ልዩ ስሙ ሠራብጥ ካህናተ ሰማይ በተባለ ቦታ በ1928 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡ ትምህርት ብፁዕነታቸው በተወለዱበት በካህናተ ሰማይ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ መምሬ […]

ዜና ዕረፍቱ ለብፁዓዊ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ሐዋርያ ዘኢትዮጵያ

ጻድቁ አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት በክብር ያረፉት ነሐሴ ፳፬ ቀን ነው። በዚህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በድምቀት ታከብረዋለች። አባታችን አቡነ ተክለ ሃይማኖት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብ እና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኃረያ ታኅሣሥ ፳፬ ቀን ፲፪፻፲፪ ዓ.ም በቡልጋ አውራጃ ኢቲሳ በሚባል ቦታ ተወለዱ፡፡ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን እሑድ ከጠዋቱ በሦስት ሰዓት ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ […]

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆስ በማኅበረ ቅዱሳን ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በመገኘት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ።

ነሐሴ 23 ቀም 2018 ዓ.ም ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆስ በማኅበረ ቅዱሳን የዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ በመገኘት አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና ሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በማኅበረ ቅዱሳን 17ኛ ዓለም አቀፍ ጠቅላላ ጉባኤ በተገኙበት ወቅት ባስተላለፉት መልእክት […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር መዋቅር እየተተገበረ መሆኑ ተገለጸ::

ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ዶግማዋን ቀኖናዋንና ሥርዓቷን በጠበቀ መልኩ መንፈሳዊ አገልግሎቷን ለማጠናከር ከምታከናውናቸው በርካታ ተግባራት መካከል ዘመኑ የደረሰበት የአይሲቲና የዲጂታል ሽግግር ሥራ ዋነኛው መሆኑ ይታወቃል:: ይህንንም ሥራ በበላይነት የሚመራና የሚያስተባብር በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት የተቋቋመው የኢንፎርሜሽንና ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ወደ ሥራ መግባቱ ታውቋል። የግንቦት […]

የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የ፳፩ኛ ዓመት በዓለ ሢመት

የዛሬ ፳፩ ዓመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ነሐሴ ፳፪ ቀን ፲፱፻፺፯ ዓ.ም በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በተካሄደው ሥርዐተ ሢመት በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት አንብሮተ እድ ፲፯ አባቶች ተሹመዋል፡፡ ከእነዚህ አባቶች መካከል ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ […]

ክፍት የሥራ ማስታወቂያ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት የሥራ መደቦች መመዘኛዎች የሚያሟሉ፤ ብቁ እና ተነሳሽነት ያላቸው 2 (ሁለት) ባለሞያ ሠራተኞችን አወዳድሮ በጽ/ቤቱ የደሞዝ ስኬል መሠረት ለመቅጠር ይፈልጋል። ማስታወቂያው የወጣበት ቀን፡ ነሐሴ 21/ 2018 ዓ.ም ማመልከቻ መቀበያ የመጨረሻ ቀን፡ መስከረም 7/2019 ዓ.ም ማመልከቻ ማቅረቢያ ሁኔታ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት በአዲሱ መዋቅር የተመረጡ የሰንበት ት/ቤቶች ሥራ አመራሮች በብጹአን አባቶች ቡራኬ አሰጠ። በተጨማሪም ለሰንበት ት/ቤት አባለት አገልግሎት የሚውል የሞባይል መተግበሪያ በይፋ አስመርቆ አስጀመረ።

በመርሐ ግብሩ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ዶክተር የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ፕሬዘደንት ፣ ብጹዕ አቡነ ጢሞጤዎስ የዳውር ኮንታ አላባና ጠንባሮ አህጉረ ስብከትሊቀ ጳጳስ መጋቢ ሀዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ በመንበረ ፖትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ […]

ቤተ ክርስቲያን የሁሉም ወገን እናት እንጂ የቡድኖች መጠቀሚያ ልትሆን አይገባም ይበቃልን እንበል!” ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕነታቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከገዳማትና አድባራት የአገልግሎት መሪዎች ጋር ባደረጉት የትውውቅ መርሐ ግብር ላይ ተገኝተው አባታዊ ቡራኬና የሥራ መመሪያ ሰጥተዋል። ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስ ያስተላለፉት ሙሉ መልእክት እንደሚከተለው ይነበባል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና […]

የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከገዳማትና አድባራት የአገልግሎት መሪዎች ጋር ትውውቅ አደረጉ።

ነሐሴ ፲፱/፳፻፲፰ ዓ/ም አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ ከነሐሴ 8 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምሮ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ኃላፊነት ተረክበው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት መመደባቸውን ተከትሎ፣ ከሀገረ ስብከቱ እና ከገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የትውውቅ መርሐ ግብር ተካሄደ። መርሐ ግብሩ ጸሎተ ወንጌል የተነበበ ሲሆን ወቦሌ ኆኅተ ብርሃን ቅድስት […]

ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ እና ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆሮስ ለ272 አገልጋዮች ሥልጣነ ክህነት ሰጡ።

ነሐሴ ፲፯ ቀን ፳፻፲፰ ዓ.ም ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን ገዳም የበላይ ጠባቂ እንዲሁም ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት በዓለምገና ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ተገኝተው ለ272 የአብነት ተማሪዎችና የቤተ ክርስቲያን […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት