የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ “በወንጌል ሕይወታችን ሆነ” በሚል ሕያው ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ “የስብከተ ወንጌል ቀን” እንዲሚያከብር ገለጸ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
«በወንጌል ኮነ ሕይወትን»
በወንጌል ሕይወታችን ሆነ
በመንበረ ፓትርያርክ ጠ/ቤ/ክ/የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ መምሪያ «የስብከተ ወንጌል ቀንን» አስመልክቶ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ፣
የስብከተ ወንጌል ቀን በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ውሳኔ መሠረት መከበር ከተጀመረ ለ3ኛ ጊዜ ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት ከሚያዝያ 18 ቀን እስከ ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ለሁለት ቀናት የሚከናወን መርሐ ግብር ነው፡፡
በመሆኑም በመጀመሪያው ቀን ማለትም ሚያዝያ 18 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ውስጥ በ8 ክ/ከተማ ቤተክህነት በተመረጡ 9 አድባራትና ገዳማት ማለትም፡-
💠በአራዳ ጉለሌ ጽ/አ/ቅ/ሩፋኤል ቤተክርቲያን
💠በየካ ክ/ከ/በየካ ደ/ሣ/ቅ/ሚካኤል ቤተክርቲያን
💠በአዲስ ከተማ በማህደረ ስብሐት ቅ/ልደታ ቤተክርቲያን
💠በኮልፌ ቀራንዮ በአየር ጤና አንቀጸ ብርሃን ኪዳነ ምሕረት 💠ቤተክርቲያን በለሚ ኩራ በጐሮ ደ/ም/ቅ/ገብርኤል ቤተክርቲያን
💠በቦሌ በገርጂ ደ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ ቤተክርቲያን
💠በአቃቂ ቃሊቲ መ/ብ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርቲያን
💠በነፋስ ስልክ በጀሞ ፈ/ዮ/ቅ/ዮሐንስና ማርያም ቤተክርቲያን
👉በሸገር ሀገረ ስብከት አድባራት ማለትም
💠በዓለም ገና ደ/ም/ቅዱስ ሚካኤል ካቴድራል
💠በወይብላ ማ/መ/ቅ/ማርያምና ቅ/ሚካኤል ካቴድራል
💠በካዬ ፈጬ ደጉ ደ/ኃ/ቅ/ገብርኤል ቤተክርቲያን ልዩ መንፈሳዊ ጉባኤያትን በማዘጋጀት በታላላቅ መምህራን ዕለቱን በማስመልከት ትምህርተ ወንጌል የሚሰጥ ሲሆን በተጨማሪም በዘማሪያን አማካኝነት በዝማሬ እ/ርን የምናመሰግንበት ቀን ይሆናል፡፡
በሁለተኛው ቀን ሚያዝያ 19 ቀን 2018 ዓ.ም ብፁዕ ወቅዱሰ አባታችን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ የቅዱስ ሊኖዶስ ዋና ጸሐፊ ብፁዕ የመምሪያው ሊቀ ጳጳስ ብፁዓን አበው ሊቀነ ጳጳሳት የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የየመምሪያውና የድርጅት የሥራ ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል ኃላፊና ም/ኃላፊ፣ የአህጉረ ስብከት የስብከተ ወንጌል ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የአዲስ አበባ የ8ቱ ክ/ከ/ቤ/ክ/ሥራ አስኪያጆችና የስ/ወ/ኃላፊዎች የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎችና የስ/ወ/ኃላፊዎች እንዲሁም የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅና የሀ/ስ/የስ/ወ/ ዋና ክፍልና ም/ኃላፊ የሰ/ት/ቤት ዋና ክፍልና የክ/ከተሞቹ ሥራ አስኪያጆችና የስ/ወ/ኃላፊዎች እንዲሁ ተጋባዥ እንግዶችና የመምሪያው አጋሮች በተገኙበት የጥናት የውይይትና የምክክር መርሐ ግብር በልዩ ሁኔታ ለሙሉ ቀን የሚካሄድ ሲሆን በመጨረሻም የጋራ የአቋም መግለጫ በማውጣት መርሐ ግብሩ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
በመሆኑም ይህን መልእክት በመከታተል ላይ የምትገኙ የሚመለከታችሁ ጥሪ የተላለፈላችሁ አካላት በተጠቀሱት ቀናትና ቦታ በሰዓቱ በመገኘት ተሳትፎ እንድታርጉና ለቅ/ቤ/ክ/የሚጠቅመውን ምክረ ሐሳባችሁን እንድትለግሱ በመምሪያው ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
በተጨማሪም በቅድስት ቤተክርስቲያን የስ/ወ/ቀን ያልሆነ ዕለት ባይኖርም በተለየ ሁኔታ ቀኑን በማሰብ የስ/ወ/አገልግሎት ተደራሽነትን ለማስፋፋት ያመች ዘንድ በሁሉም አገልጋዮችና አማኞች ዘንድ የወንጌልን እውነት ለማስረፅ የተደረገ /የተዘጋጀ/ መርሐ ግብር ነው፡፡
በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ እያስገነዘብን በተለይም በሚዲያ ሥራ ላይ ተስማርታችሁ የምትገኙ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ልጆች በጉባኤያቱ ቦታዎች ላይ በመገኘት የሚዲያ ሽፋን እንድትሰጡልንና የስ/ወ/ተደራሽነትን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥራያችንን በድጋሜ በቤተክርስቲያን ስም እናስተላልፋልን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር