አዲስ ለተመደቡት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ብርሃን ሰሎሞን በቀለ አቀባበል ተደረገላቸው።
በመርሐ ግብሩ ንቡረ ዕድ ኤልያስ አብርሃ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክልት ሥራ አስኪያጅ፣ መልአከ ሰላም ዶ/ር አባ ቃለጽድቅ ሙሉጌታ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ዋና ሐላፊ፣ የሀገረ ስብከቱ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱና የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሠራተኞች ተገኝተዋል።