ለአይሲቲ እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዙርያ ሥልጠና ተሰጠ፡፡
23 ቀን 2018 ዓ.ም አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያበመንበረ ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ለአይሲቲ እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዙርያ ስልጠና ተሰጠ፡፡
በስልጠናው የአባቶች እና የቤተክርስቲያንን ክብርንና ገፅታ የማይገነቡ መስሎችን ከማጋራት መቆጠብ እንደሚገባ ተገልጿል።
በሥልጠናውን ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ, የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን መድኃኔዓለም ገዳም የበላይ ኃላፊ እና ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የልማት እና ክርስቲያነዊ ተራድዖ ኮሚሽን ሊቀ ጳጳስ በጸሎት አስጀምረዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መንበር ፖትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ለአይሲቲ እና ለሚዲያ ባለሙያዎች ያዘጋጀውን ሥልጠና የሰጡት የራዕይ ሕጻናት መረጃ ድርጅት መሥራች እና ዳይሬክተር እንዲሁም ኮምፒውተር ኔትወርክ እና ሳይበር ደኅንነት ባለሙያ በሆኑት ፕሮፌሰር ጽጌ ጥበቡ አማካኝነት ነው።
ብፁዓን አባቶች አሰልጣኟ ቤተክርስቲያን ዘመኑ በፈጠረው ቴክኖሎጂ እንድትዘመን በማሰብ እንደ ቤተክርስቲያን ልጅነቷ በራሷ ተነሳነት ማገዝ አለብኝ በማለት ይህን ሥልጠና በመስጠታቸው አመስግነዋል።
የሥልጠናው አላማ የሰው ሠራሽ አስተውሎትን በመጠቀም ከሐሰተኛ የጹሑፍ እና የድምፅ መልክቶች እንዴት ራሳችን በመከላከል ሀገራችንም ሆነ ቤተክርስትያናችንን ደኅንነት እና ገጽታዋን በመልካም ጎን ለማሣየት በጥንቃቄ መሥራት እንደሚገባ ፕ/ር ጽጌ ገልጸዋል ።
በተለያዩ መልኩ የሚከሰቱ የሳይበር ጥቃቶችን ለመከላከል በሚቻልበት መንገድ ሥልጠናው በትኩረት ተሰጥቷል፡፡
በAI ተጠቃሚ ለመሆን ትክክለኛውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ትምህርት ወደ መረጃ ቋት በማስገባት ለሌሎቹ ተደራሽ እንዲሆን ለማድረግ እንደሚገባ እና እምነቱን ለዓለም ሁሉ ተደራሽ እንዲሆን በትጋት መሥራት እንደሚገባ ፕ/ር ጽጌ አሳስበዋል።
በሥልጠናው ላይ ከኢኦተቤ ሕብ ግንኙነት መምሪያ ፣ከአይቲና ኢንፎርሜሽን አገልገልቶት መምሪያ ፣ከኢኦተቤ ቴቪ፣ ከኢኦተቤ አፋን ኦሮሞ ቴቪ ፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልገሎት እና ሕዝብ ግንኙነት እንዲ አይሲቲ ክፍሎች ተውጣጡ የ ጋዜጠኞችና የቴክኒክ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።
©ኢኦተቤ ቴቪ
