• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

“ሃይማኖት በአፍ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ የምንቀበለው እውነታ ነው።” ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 13ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዓድዋ ሙዚየም ሕንጻ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄዷል። ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ፣ ሀዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ “ሃይማኖት በአፍ የሚነገር ብቻ ሳይሆን በልብ የሚታሰብ የምንቀበለው እውነታ ነው።” በማለት የሃይማኖትን ከፍታ አንስተዋል። ብፁዕነታቸው የሃይማኖትን ምንነት ከቃሉ የት […]

“በጋራ በመወያየት ችግሮችን መፍታትና የተሰጠንን ሐላፊነት ለቤተ ክርስቲያን ለጥቅም ማዋል እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ አሳሰቡ

በጋራ በመወያየት ችግሮችን መፍታትና የተሰጠንን ሐላፊነት ለቤተ ክርስቲያን ለጥቅም ማዋል እንደሚገባ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ አሳሰቡ። ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባዘጋጀው የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ላይ ነው። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከመስከረም 26_30/2018 ዓ/ም ለተከታታይ 5 ቀናት ለሀገረ ስብከቱ፣ ለክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት እንዲሁም ለገዳማትና አድባራት የሥራ ሐላፊዎችና ሠራተኞች ያዘጋጀው የሥልጠናና […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንና ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ እና ሐዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ የቦርድ ሰብሳቢ ዛሬ መስከረም 22/2018 ዓ.ም የቦሌ ቡልቡላ ፍኖተ ሕይወት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት እየገነባ የሚገኘውን አዲስ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንና ልዩ ልዩ የልማት ሥራዎችን ጎበኙ ። የደብሩ የአገልግሎት መሪዎች እየተገነባ በሚገኘው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ዙሪያ […]

የሥልጠናና የምክክር ጉባኤ ጥሪ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተሻለ የአመራር ለውጥ ማስመዝገብ ይቻል ዘንድ ለሀገረ ስብከቱ፣ ለክፍለ ከተማ፣ ለገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከመስከረም 26-30 ቀን 2018 ዓ.ም የሥልጠናና የምክክር መርሐ ግብር ተይዟል ፡፡ በዚህ መርሐ ግብር መሠረት በሥልጠናውና በምክክሩ የሚሳተፉ አካላት 1. በ26/01/2018 ዓ.ም የሀገረ ስብከታችን የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎችና ምክትል የክፍል ኃላፊዎች፣ የክፍለ ከተማ ቤተክህነት ጽ/ቤት ሥራ […]

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰጠ የኃዘን መግለጫ

መስከረም 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 1፡45 በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በአረርቲ ከተማ በምትገኘው የደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ዓመታዊውን የቅድስት ድንግል ማርያም ክብረ በዓል በማክበርና አዲስ እየተሠራ ያለውን ሕንጻ ቤተክርስቲያን በመጎብኘት ላይ የነበሩ ወገኖቻችን የሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑ ርብራብ ተደርምሶ ሕይወታቸው በማለፉና የአካል ጉዳት በመድረሱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት የተሰማው ኃዘን ጥልቅ ነው፡፡ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማዕከልን ጎበኙ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የሰንሻይን ፊላንትሮፊ ፋውንዴሽን የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማዕከልን ጎበኙ። ኢትዮጵያዊ አብሮነትንና ሰብአዊ መተሳሰብን እንዲሁም ኅብረታዊ አንድነት መሠረት ያደረገ ነው የተባለው ሰንሻይን የአረጋውያን መጦሪያና መንከባከቢያ ማዕከልን ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በቦታው ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል። ከብፁዕነታቸ ጋር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ […]

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ ከአዲስ አበባ ከተማ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ። በመርሐ ግብሩ ላይ የመንበረ ፓትሪያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ እንዲሁም የአዲስ አበባና የሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ እና የመስቀል በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ በተገኙበት ከአዲስ […]

ተቀጸል ጽጌ በዓል ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጬጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት በተገኙበት ተከብሯል

መስከረም ፲/፳፻፲፰ ዓ/ም በየዓመቱ መስከረም ፲ ቀን በጥንት ጊዜ ወርኃ ክረምቱ አለፈ የጽጌ ዘመን መጣ ይህን ያደረገ እግዚአብሕር ይመስገን ሲሉ ተቀጸል ጽጌን መስከረም ፳፭ ቀን በታላቅ የምስጋና ማዕድ በቤተ ክርስቲያንንና ነገሥታቱ አብያተ መንግሥት ይከበር ነበር። በኋላ አጼ ዳዊት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበትን ግማደ መስቀል ከግብጽ ወደ ኢትዮጵያ መስከረም ፲ ቀን በመግባቱ ምክንያት መስቀል ከሁሉም ነገር […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ያለፉት 100 ቀናትና ሥራዎቹ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙ ጥንታውያት አህጉረ ስብከት መካከል አንዱ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ነው። ሀገረ ስብከቱ በሥሩ 8 ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት፣ ከ260 በላይ አብያተ ክርስቲያናት፣ ከ30,000 በላይ አገልጋዮችና ሠራተኞች፣ በርካታ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ሰንበት ተማሪዎች፣ እጅግ ብዙ ደጋግ ኦርቶዶክሳውያን የሚገኙበት ታላቅ ሀገረ ስብከት ነው። ሀገረ ስብከቱን በርካታ ብፁዓን […]

“ከምክርቤት እስከ መምሪያ” የስብከተ ወንጌል አገልግሎት መዋቅር

ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋ እና የሸገር አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የምስካየ ኅዙናን ገዳም የበላይ ኀላፊ፣ የቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ ቦርድ ሰብሳቢ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሓፊ፣ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ የማኅበራት ማደራጃ መምሪያ እና የቤተ መጻሕፍት ወመዘክር መምሪያ የበላይ ኀላፊ ክቡር ንቡ እድ ኤልያስ አብርሃ የመ/ፓ/ጠ/ቤ/ክህነት ጽ/ቤት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት