• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ሀገር ጠቀምና ትውልድ ተኮር ሥራዎችን በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ

ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ሀገር ጠቀምና ትውልድ ተኮር ሥራዎችን በጋራ መሥራት እንደሚገባቸው ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ገለጹ። በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት በ 2017 ዓ.ም በነበረው የአገልግሎት አፈጻጸም ከክፍለ ከተማው ቤተ ክህነት ጋር በጋራ ሲሠሩ ለነበሩ ባለድርሻ አካላት የምስጋና መርሐ ግብር ነሐሴ 18 በቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል የስብከተ ወንጌል አዳራሽ […]

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ የዕረፍት መታሰቢያ ሥርዓተ ጸሎት ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናወነ

የብፁዕ ወቅዱስ ዶ/ር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት የዕረፍታቸው መታሰቢያ የጸሎት መርሐ ግብር በመንበረ ጽባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተከናውኗል። ‎በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የምስካየ […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ

የብፁዕ ወቅዱስ ዶክተር አቡነ ጳውሎስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ፤ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዚደንት፣ የዓለም ሃይማኖቶች ምክር ቤት ለሰላም የክብር ፕሬዚደንት፣ የዓለም የሰላም አምባሳደር፤ 13ኛ ዓመት ዕረፍት ነሐሴ 10 ቀን 2017 ዓ.ም በመንበረ ጻባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በደማቅ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የጾመ ፍልሰታ ለማርያም መግባትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ ቃለ በረከትና ለአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት መመሪያ አስተላለፉ

ብፁዕነታቸው ሱባኤው በሥርዓትና መልስ ሊያስገኝ በሚችል መልኩ መከናወንን እንዳለበት አሳስበዋል። በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። በመላው ዓለም የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮች ምእመናንና ምእመናት እንኳን ለ፳፻፲፯ ዓ/ም ጾመ ፍልሰታ ለማርያም በጤና አደረሳችሁ። “ተመየጡ ኀቤየ ወተሐይዉ በጾም ወበጸሎት ወበርትዕት ሃይማኖት “በጾም በጸሎት በእውነተኛ ሃይማኖትም ወደ እኔ ተመለሱ ትድናላችሁም” ቅዱስ ያሬድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሐዶ ቤተ ክርስቲያን […]

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ.ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ የ2017 ዓ/ም የጾመ ፍልሰታ መግባትን አስመልክተው ቃለ ምእዳንና ቡራኬ ሰጥተዋል። መግለጫው የሚከተለው ነው። መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፡- በስመ ኣብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሓዱ ኣምላክ ኣሜን፤ በሀገራችን በኢትዮጵያና በመላው ዓለም የምትገኙ ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፡- የክብር ባለቤት እግዚአብሔር ኣምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ […]

መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በነበሩበት ጊዜ የሰጡትን አባታዊ አገልግሎት አስመልክቶ የምስጋና መርሐ ግብር ተካሄደ

ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና ሥራ አመራር መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ የቅዱስ ሲኖዶስ ቋሚ አባል እንዲሁም የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት የሥራ አስፈጻሚ ቦርድ ሰብሳቢ በተገኙበት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ለተመደቡት ክቡር መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንገሤ በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስሊቀ ጳጳስ ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ በመመረቂያ ጋውን ጸሎተ ቅዳሴ ላከናወኑት ካህንና የደብሩ አለቃ አስተዳደራዊ ርምጃና ቀኖና ሰጡ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ ከሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ “በመመረቂያ ጋውን” ጸሎተ ቅዳሴ ላከናወኑት ካህንና የደብሩ አለቃ አስተዳደራዊ ርምጃና ቀኖና ሰጡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅድሳት መጻሕፍትን መሠረት፣ ትውፊትን እንደመቀነት ቀኖናን እንደአጥር አድርጋ ሥርዐተ አምልኮን እስካሁን ባለመለወጥ እያከናወነች የምትገኝ ድንቅና ጥንታዊት ቤተ ክርስቲያን ናት። ይሁንንና መነሻቸው የተለያየ ሆኖ በአሁኑ ጊዜ በሰማይ ሥርዐት በመላእክት ምስጋና […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የውስጥ ቢሮዎች ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተመረቀ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የውስጥ ቢሮዎች ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ አቡነ ሳዊሮስ ሊቀ ጳጳስና በብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ አቡነ ዲዮስቆሮስ ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ ተመረቀ ። የሀገረ ስብከቱ ዋና መሥሪያ ቤት ቀደም ሲል ብፁዕ አቡነ መቃርዮስ ሊቀ ጳጳስ በሰአሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ለመሥራት አቅደው ባይሳካም በኋላ ብፁዕ አቡነ ሳሙኤል በአዲስ አበባ ሀገረ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በደብሩ የተሠሩት የልማት ሥራዎች አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ባረኩ

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባና ሀዲያ ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው በደብሩ የተሠሩት የልማት ሥራዎች አገልግሎት ይሰጡ ዘንድ ባረኩ። ከብፁዕነቻው ጋር የሀገረ ስብከቱ ዋና ስራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤና የሀገረ ስብከቱ የሥራ ኃላፊዎች አብረው ተገኝተዋል። ብፁዕነታቸው የመጀመሪያውን ጉብኝት በአቃቂ ደብረ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ […]

“150 ተፈናቃይ አገልጋዮችን” በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሥራ መድቦ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ

በቋሚ ቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነላቸውን “150 ተፈናቃይ አገልጋዮችን” በተመለከተ ሀገረ ስብከቱ ወደ ሥራ መድቦ ለማጠናቀቅ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑ ተገለጸ። ዛሬ ከሰዓት በኋላ በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ መሪነት የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ፣ የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች፣ የክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገረ ስብከቱና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት