በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የገነተ ልዑል ቅዱስ ጊዮርጊስ መቃኞ ቤተክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ ።
ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ሰኔ ፮/፳፻፲፰ ዓ/ም
በአዲስ አበባ ሀገረ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፉሪ ሠፈራ አካባቢ በምትክ በተሰጠ በ3 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈው ገነተ ልዑል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን መቃኞ ተባርኮ አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።
ይዞታውን ለማግኘት ከሰባት ዓመት በላይ የወሰደው የዚህ አዲስ ቤተክርስቲያን ቡራኬ መርሐ ግብር ላይ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ነጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ዕለቱን አስመልክተው ትምሕርተ ወንጌል ተሰጥተዋል ።
መልአከ ምሕረት በቃሉ ያለው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት የትምህርት ክፍል ምክትል መምሪያ ኃላፊ ባስተላለፉት መልእክት ይህ ቤተክርስቲያን ሲገነባ ብዙ ዋጋ ተከፍሏል ያሉ ሲሆን ለዚህ ሥራ መሳካት ዋጋ ለከፈሉ አገልጋዮች በሙሉ ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል ።
በሥነ ሥርዓቱ የድብሩ አስተዳዳሪ መልአክ ሕይወት ቀሲስ ዘለዓለም ተስፋዉን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ ምዕመናን ተገኝተዋል።
የዚህ ታላቅ ቤተክርስቲያን መታነጽ በአካባቢው ምዕመናን ሲቀርብ የነበረውን የጸሎትና የሱባኤ ቦታ ጥያቄ በከፍተኛ ደረጃ የሚመልስ ከመሆኑም በላይ፣ ለሰፈሩ ሰላምና አንድነት ትልቅ አስተዋጽዖ እንደሚኖረዉ መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ ገብረመድኅን ንጉሤ ገልጸዋል ።
ቤተክርስቲያኑ ተጠናቆ ለዚህ የተቀደሰ ዕለት እንዲበቃ በገንዘባቸው፣ በዕውቀታቸውና በጉልበታቸው ድጋፍ ለደረጉ ምዕመናንና ይገባል ሲሉ የደብሩ አስተዳዳሪ የምስጋና መልዕክት አስተላልፈዋል ።
EOTC TV
