የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የ9 ወራት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ላይ ውይይት አደረገ
በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የቦርድ ሰብሳቢነት የተመረው የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በዛሬ ዕለት መደበኛ ሰብሰባውን አድርጓል።
በስብሰባው ላይ ብፁዕነታቸውን ጨምሮ የጉባኤው የቦርድ አባላት የየ ቤተ እምነቱ መሪዎችና ተወካዮች አባቶች ፣ መጋቢ ታምራት አበጋዝ የጉባኤ ዋና ጸሐፊ ተገኝተዋል።
በሁሉም ሃይማቶች “ወርቃማው ሕግ ተብሎ በሚጠቀስው የፍቅርና የመከባበር ሕግ መሠረትነት በአብሮነትና የሰውነት ልክን ዐቢይ ጉዳይ በማድረግ እንዲሚያገለግል የሚታመነው የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ እንደሚገኝ ይገለጻል።
በተለይም ጥቅምት 2003 ዓ/ም የተመሠረተው ይህ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተለያየ እምነት ያላቸውን አካላት በአንድነት በሚያሰማራቸው የሰዎች አብሮነትና የማይለወጡ ተፈጥሯዊ ገጾችን ለመጠበቅና ለማክብር የተቋቋመው ጉባኤው በተቻለ አቅም እየተንቀሳቀሰም ይገኛል ተብሏል።
በዚሁም የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በከተማው የተጣለበትን ኃላፊነት ለመወጣት የተቻለውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
በዛሬ ዕለትም በነበረው የዘጠኝ ወራት የሥራ አፈጻጻም ውይይት ያደረገ ሲሆን በሰላምና በአብሮነት እንዲሁም በማኅበረሰባዊ መልካም ግንኙነት ልማት ላይ ውይይት መደረጉ ተገልጿል።
በቀጣይም ስለሚሠሩ ሥራዎችና የሚጠበቁ ውጤቶች ላይ ማብራሪያ የቀረበ ሲሆን አቅጣጫ በማስቀመጥ ስብባው መጠናቀቁን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
በተያዘው ዜና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ አመራሮች የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩትን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ኢንስቲትዩቱ ያለውን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ የሚያስቃኝ ገለጻ የተደረገላቸው ሲሆን ተቋሙ በሰው ሰራሽ አስተውሎት የታገዙ የፈጠራ ሥራዎችን በማበልጸግ በሀገሪቱ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት ላይ አስተዋጽዖ እያበረከተ መሆኑም ተገልጿል።
የሃይማኖት አባቶች በበኩላቸው በተመለከቱት ነገር መደነቃቸውን ገለጸው ተቋሙ ችግር ፈቺ የቴክኖሎጂ ውጤቶች የሚበለጽግበት እና ለትውልድ የሚተላለፍ አቅም ያለበት ስፍራ መሆኑን ገልጸው እየተሠራ ያለውን ሥራ አድንቀዋል።
በተቋሙ ለተደረገላቸው አቀባበል እና መስተንግዶ ምስጋና አቅርበዋል።
የአ/አ/ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ሕዝብ ግንኙነት
