• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ።

የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል ባሕረ ጥምቀት ቦታ የተለያዩ አገልግሎቶችን እንዲሰጥ ሥራዎች መጀመራቸው ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቦሌና ለሚኩራ ክፍላተ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የቦሌ ደብረ ሳሌም መድኃኔዓለም ካቴድራል የባሕረ ጥምቀት ከተማ አስተዳዳሩ ከሚከተለው የኮሪደር ልማት ጋር በተገናዘበ መልኩ አገሎግሎት የሚሰጡ የተለያዩ ፕሮጆክቶች እንደሚሠሩበት የክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት […]

ለቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ የወሰን ችካል ለመቸከል በትናትናው ዕለት ተይዞ የነበረው መርሐ ግብር መስተጓጎሉ ተገለጸ።

ለቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ የወሰን ችካል ለመቸከል በትናንትናው ዕለት ተይዞ የነበረው መርሐ ግብር መስተጓጎሉ ተገለጸ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ያሬድ የዜማ ኮሌጅ ቦታ አቅርቦት እንዲዘጋጅላቸው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ ሚያዚያ 5/2013 ዓ/ም ከተወሰነላቸው የቦታ ጥያቄዎች መካከል አንዱ እንደነበር ሰነዱ ያስረዳል። ከዚያም ጊዜ ጀምሮ ከተማ አስተዳደሩ የቦታ አቅርቦቱ እንዲዘጋጅ በንፋስ ስልክ ላፍቶና በለሚ […]

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይን በተመለከተ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አጥኝ ኮሚቴ መሠየሙ ተገለጸ።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይን በተመለከተ በብፁዓን አባቶች የሚመራ አጥኝ ኮሚቴ መሠየሙ ተገለጸ የጥቅምቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ለውይይት ከያዛቸው 28 አጀንዳዎች መካከል በተራ ቁጥር 5 እና 6 የሚገኙት ሀገረ ስብከቱን የሚመለከቱ ጉዳዮች ነበር። በዚህ መነሻነት ጉባኤው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት አማካኝነት የተሰይመው አጥኝ ኮሚቴ በሀገረ ስብከቱ ያሉ ችግሮችና መፍትሔዎች […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በትናንትናው የእሳት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች አጋርነቱን ገለጸ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስቅዱስ በትናንትናው ዕለት ጥቅምት ፲፩ ቀን ፳፻፲፯ ዓ/ም በአዲስ አበባ ከተማ መርካቶ ገበያ ሸማ ተራ በተባለው አካባቢ በደረሰው የእሳት አደጋ ጉዳት ለደሰባቸው ወገኖች ባስተላለፉት መልእክት በደረሰው የሃብትና ንብረት ውድመት የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸው። በአደጋው […]

“#ሕዝቡም ሊያደምጠንና ሊከተለን የሚችለው መስለን ሳይሆን ሆነን ስንገኝለት ነው” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! •ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የባሕር ዳርና የሰሜን ጐጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ •ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፤ •ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት፤ ዓመቱን ጠብቆ ስለ አጠቃላይ ተልእኮአችን ለመወያየት በዚህ ጉባኤ የሰበሰበን […]

በሀገረ ስብከቱ የሚገኙ ሰባክያነ ወንጌል በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ በቀጣይ ሳምንት ሰኞና ረቡዕ ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰባክያነ ወንጌል በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ ሰኞ ጥቅምት 11 ቀን እና ረቡዕ ጥቅምት 13 ቀን 2017 ዓ/ም በየክፍላተ ከተሞቻቸው ውይይት እንደሚያደርጉ ተገለጸ። የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልእኮ ዋና ክፍል የተጣለበትን አደራ ለመወጣት እና በወንጌል አገልግሎቱ ዙሪያ ለውጥ ለማምጣት የተለያዩ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። በተለይም ደግሞ በሀገረ ስብከቱ ውስጥ ባሉ ገዳማትና […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባሳለፍነው ዓመት ከ631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በማስገባቱ ከፍተኛ ተሸላሚ ሆነ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ፵፫ኛው የመንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ለጥቅምት ፬/፳፻፲፯ ዓ/ም ጀምሮ ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለት ተጠናቋል። በማጠናቀቂያ መርሐ ግብሩ በየዘርፉ አህጉረ ስብከትን በማወዳዳር የእውቅናና ሽልማት መርሐ ግብር ተከናውናል። ከማወዳዳሪያ ዘርፎቹ መካከል አንዱ ከፍተኛ አጽተዋጽኦ በማስገባት ዘርፍ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት 631 ሚሊዮን ብር በላይ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት […]

የአቋም መግለጫ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የ፵፫ኛው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ የአቋም መግለጫ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይነበባል። “ትውልደ ትውልድ ይንእዱ ምግባሪከ ወይዜንዉ ኃይለከ – የልጅ ልጅ ሥራህን ይናገራሉ፤ ያመሰግናሉ፣ ከሃሊነትህን ይናገራሉ ያስተምራሉ” መዝ 144 ቁ 4 ጥንታዊት፣ ሐዋርያዊት፣ ዓለምአቀፋዊት የሆነቸው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሐዋርያዊ ተልዕኮዋ ረጅም ዘመናትን ሰማያዊውን ጥበብንና ምድራዊውን ዕውቀትን […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ ማድረጉ ተገልጸ።

ሦስተኛውን ቀን የያዘው በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 43ኛ መንበረ ፓትርያርክ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የየአህጉረ ስብከቱ ዓመታዊ የአገልግሎት አፈጻጸም ሪፖርቶች እየቀረቡ ይገኛሉ። ከነዚህ በአዲስ የተቋቋመው የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ሪፖርት ያቀረበ ሲሆን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ባደረገው ድጋፍ በቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት የተዘጉ 9 አብያተ ክርስቲያናት እንዲከፍቱ አድሮጓል በለዋል። የቡኖ በደሌ ሀገረ ስብከት ድጋፍ […]

የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል።

የ፵፫ ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዓለም አቀፍ አጠቃላይ ሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ተጀምሯል። ጉባኤ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ርእሰ መንበርነት እየተመራ ይገኛል። ቅዱስነታቸው የመክፈቻ መልእክት አስተላልፈዋል። ብፁዕ አቡነ አብርሃም የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክሆነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባሕር ዳርና […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት