• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

“ወይደልወነ ከመ ንፈጽም ኵሎ ጽድቀ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናል ” (ማቴ. 3፡15)

ለመላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላት እንኳን ለ2018 ዓ.ም በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ፡፡ በማቴዎስ ወንጌል ተጽፎ የሚገኘውና ከላይ መነሻችን ያደረግነው ቃል ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለመጥምቁ ዮሐንስ የነገረው ቃል ነው፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ እርሱ በጌታ ሊጠመቅ እንጂ እርሱ ጌታውን ለማጥመቅ እንደማይችል በትሕትና በመግለጽ ሊከለክለው እየሞከረ ነበር፡፡ ጌታችን ግን፣ ወይደልወነ ከመ ንፈጽም ኵሎ ጽድቀ ጽድቅን ሁሉ […]

“እግዚአብሔርን አምኖ መኖር ሕይወታችን ባቢሎን እንዳይሆን የሚጠብቅ የልብ ማረፊያ በመሆኑ እርሱን በማመን ልጸና ይገባል። ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ

“እግዚአብሔርን አምኖ መኖር ሕይወታችን ባቢሎን እንዳይሆን የሚጠብቅ የልብ ማረፊያ በመሆኑ በእንምነት ልጸና ይገባል በማለት ብፀለዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕነታቸው ይህንን ያሉት የቅድስት ሥላሴ ዓመታዊ ክብረ በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል በዛሬው ዕለት በተከበረበት በዓል ላይ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በዓላት የምታከብርባቸው መሠረታዊ ጉዳይ ከመዳን ጋር ግንኙነት ባለው መልኩ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የ2018 ዓ/ም የጥምቀት በዓል የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በተመለከተ ውይይት አደረገ

በየዓመቱ የሚከበረውን የጌታችን የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን በዓለ ጥምቀት አስመልክቶ ሀገረ ስብከቱ ከሚመለከታቸው የሥራ ሐላፊዎች ጋር በቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ላይ ውይይት አድርጓል። በዛሬው ዕለት በሀገረ ስብከቱ አዳራሽ የተደረገው ውይይት በመልአከ ምሕረት አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መሪነት የተከናወነ ሲሆን የሀገረ ስብከቱ ምክትል ሥራ አክኪያጅና የዋና ዋና ክፍል ሐላፊዎች ፣ የክፍለ ከተማ ቤተ […]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በተለያዩ ቦታዎች ለምታስገነባቸው ሁለገብ ሕንጻዎች ከአሸናፊ ኮንትራክተሮች ጋር የግንባታ ሥራ ስምምነት ተፈራረመች

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በኮሪደር ልማት ምክንያት በፈረሱና ከመንግስት በተሰጧት ቦታዎች ላይ ሁለገብና ዘመናዊ ሕንጻዎችን በማስገንባት በአስቸኳይ አገልግሎት ላይ እንድታውል የቅዱስ ሲኖዶስምልአተ ጉባኤ በግንቦቱ ርክበ ካህና ወቅት ያስተላለፈውን ውሳኔ ተከትሎ በፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አሶኪያጅ፣የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ […]

ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ ሊቀ ጳጳስ የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም የማሰልጠኛዉን ደረጃ ለማሳደግ ለ G+5 ሕንጻ መሠረት ድንጋይ ባርከው አስቀመጡ

የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም የማሰልጠኛዉን ደረጃ ለማሳደግ G+5 ሕንጻ መሰረት በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ሀዲያና ስልጤ አኅጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ጥር 4 ቀን ተቀምጧል። የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም በብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ መመሪያ ሰጪነት አዲስ በማስገንባት ላይ የሚገኘውን ግዙፍ የማሰልጠኛዉ ማስፋፊያ ሕንፃ የግንባታ ሥራው በአጭር ጊዜ ተገንብቶ ለአገልግሎት ክፍት መሆን እንዳለበት ዲያቆን ኢንጅነር ለዓለም ጥላሁን […]

የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም ለአራተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን ፳፮ (26) ደቀ መዛሙርት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ በተገኙበት አስመረቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሀዲያና ስልጤ ሀገረስብከት የሚገኘው የሆሣዕና ካህናት ማሰልጠኛ ተቋም በዛሬው ዕለት ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ የአዲስ አበባ ፣ ሀዲያና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ከተለያዩ ወረዳ ቤተ ክህነቶች የተወጣጡ 26 ደቀ መዛሙርትን ለሦስት ወራት በተለያዩ የቤተ ክርስቲያን አስተምህሮዎች ዙሪያ ሥልጠና ሲወስዱ ለቆዩት ሠልጣኞች የምርቃት መርሐ ግብር በሀገረ ስብከቱ በስብከተ ወንጌል አዳራሽ አከናውኗል። […]

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽ/ቤት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር አካሄደ።

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ጽሕፈት ቤት በየዓመቱ በበዓለ ልደት፣ በበዓለ ፋሲካና በዘመን መለወጫ በዓል ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር እንደሚያከናውን የሚታወቅ ነው። በዚሁ መሠረት የ2018ዓ.ም. የጌታችንና የመድኀኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን የልደት በዓል አስመልክቶ በዛሬው እለት የእንኳን አደረሰዎ መርሐግብር የተካሄደ ሲሆን በመርሐግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሸገር ከተማና የደቡብ ምዕራብ […]

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጰሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ዘተናገረ በበዓለ ልደቱ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ዘዕሥራ ምእት ዓሠርቱ ወሰምንቱ ዓመት ምሕረት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ኣሐዱ ኣምላክ አሜን! + በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣ + ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፣ + የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፣ + በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፣ + እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፣ እኛ በሕይወት እንኖር ዘንድ አንድ ልጁን ወደ ዓለም የላከ እግዚአብሔር […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በጎርጎርዮሳውያን /Gregorians/ የዘመን አቆጣጠር በነገው ዕለት የሚጀመረውን የ2026 አዲስ ዓመት በማስመልከት ለመላው የዓለም ማኅበረሰብእ አባታዊ መልእክት አስተላለፉ

ቅዱስነታቸው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ያስተላለፉት አባታዊ መልእክት የአማርኛ ትርጉም እንደሚከተለው ቀርቧል፦ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ለመላው የዓለም ሕዝብ የተላለፈ አባታዊ መልእክት በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! “እስመ ናሁ ተወልደ ለክሙ ዮም መድኅን ዘውእቱ ክርስቶስ እግዚእ ቡሩክ በሀገረ ዳዊት፡- እነሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኅን ተወልዶላችኋል፤ ይኸውም ቡሩክ ጌታ ክርስቶስ ነው።” (ሉቃ. 2፡11) የጌታችን ልደት የሰው […]

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መግለጫ

ከሰሞኑ በአገልጋይ ሄኖክ (በጂፕኤስ) ቴሌቬዠን የተላለፈው መልዕክት የተከበረውን የሰላሌን ማህበረሰብ የማይመጥን እና አጠቃላይ የማህበረሰባችንን መልካም ባህሎችና እሴቶቻችንን የማይወክል መልዕክት በመሆኑ ጉባኤያችን ይህንን ተግባር በፅኑ ያወግዛል። እንዲህ አይነት ተግባራት መጠኑና ይዘቱ ይለያይ እንጂ በሁሉም የእምነት ተቋማት አከባቢ የሚስተዋሉ ችግሮች ናቸው። እንደዚህ አይነት በሃይማኖት ተቋማት ስር ተጠልለው የጥላቻ ንግግሮችንና፣ መልዕክቶችን የሚያስተላልፉ ግለሰቦች የጥላቻ ንግግሮችን በሶሻል ሚዲያ ማስተላለፍ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት