የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትቤቶች አንድነት በአዲሱ መዋቅር የተመረጡ የሰንበት ት/ቤቶች ሥራ አመራሮች በብጹአን አባቶች ቡራኬ አሰጠ። በተጨማሪም ለሰንበት ት/ቤት አባለት አገልግሎት የሚውል የሞባይል መተግበሪያ በይፋ አስመርቆ አስጀመረ።
በመርሐ ግብሩ ብጹዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ዶክተር የደቡብ ኦሞ እና አሪ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የቅድስት ሥላሴ ፕሬዘደንት ፣ ብጹዕ አቡነ ጢሞጤዎስ የዳውር ኮንታ አላባና ጠንባሮ አህጉረ ስብከትሊቀ ጳጳስ መጋቢ ሀዲስ ኃይለ እግዚእ አሰፋ በመንበረ ፖትርያሪክ ጠቅላይ ቤተክህነት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በጠቅላይ ቤተክህነት የሊቃውንት ጉባኤ ምክትል ኃላፊ፣ መምህር ደምስ አየለ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ ዋና ክፍል ኃላፊ፣ ላዕከ ሔራን መንክር ግርማ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ ጥሪ የተደረገላችው እንግዶች ፣ የሀገረስብከት፣ የክፍለከተማ እና የቀድሞ እና አዲስ የተመረጡ የገዳማት እና አድባራት ሰንበት ት/ቤት አመራሮች በተገኙበት መርሐግብሩ ተካሂዷል።መርሐ ግብሩ በቦሌ መድኃኔዓለም ካቴድራል አዳራሽ የተከናወነ ሲሆን በብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ዶ/ር መሪነት በካቴድራሉ ካህናት ጸሎተ ወንጌል የደረሰ ሲሆን በመርሐ ግብሩ መጀመሪያ ዲያቆን ዶ/ር አንዷለም ኃይሉ የአዋሽ ካፒታል ፕሬዘደንት እና የደብረይድራስ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሰንበት ት/ቤት አባል እና የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀመንበር በሰንበት ትቤት እና በሴኩላር ዓለም ያላቸውን የካበተ ልምዳቸውን የጉባኤው ዋና ተናጋሪ “key not speech” ለአመራሩ በሚመሩበት ዘመን እና በህይወታቸው መርህ አድርገው የሚወስዱት ከፍተኛ ልምድ ሊሰጡ የሚችሉ ሀሳቦችን አካፍለዋል።
ከዛም በመቀጠል የካቴድራሉ ሰንበት ት/ቤት ዝማሬ ከቀረበ በውኃላ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ተቀዳሚ ምክትል ሰብሳቢ የእለቱን መልእክት ያስተላለፈ ሲሆን በመልእክቱም
የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የመዋቅር ትግበራውን ከግንቦት አንድ አስከ ሰኔ 30 2018 ዓ.ም በገዳማትእና አድባራት የሰንበት ት/ቤቶች የሥራ አመራር ምርጫ ሲያከናውን መቆየቱን።
በምርጫው ከ233 በአዲስ አበባ ካሉ መምረጥ ከሚችሉ ሰንበት ትቤቶች 229 ሰንበት ትቤቶች ከ2400በላይ አዲስ አመራሮች መመረጣቸውን አብራርቷል።
እነዚህ አዲስ አመራሮችም በአራት ርዕሰ ጉዳይ የአራት ሳምንት የ16 ሰዓታት ስልጠና መሰጠቱ ገለጸዋል። በተጨማሪ ይህ መርሐ ግብር የቀደሞ የሰንበት ት/ቤቶች አመራር አባላት ለመዋቅርትግበራው በአመራርነታቸው ተፈጻሚ እንዲሆን ለአደረጉት ከፍተኛ አመራር እና መንፈሳዊ ትጋት ምስጋና ለአዲስ ተመራጮች ቀጣዩ አገልግሎት በቀደመ ልማድ ሳይሆን እንደቤተክርስትያን እቅድ እንዲያገለግሉ አደራ እና የሥራ ማስጀመሪያ በብጹአን አባቶች ጸሎተ ቡራኬ እና አባታዊ መመርያ ለመስጠት የተዘጋጀ መርሐ ግብር መሆኑን ገልጸዋል።
ከዛም በመቀጠል ብጹዕ አቡነ ፊሊጶስ ዶ/ር አመራር እና አገልግሎት በሚል ርእስ ስለአመራርነት ሰፊ ትምህርት የሰጡሲሆን አመራር ይወለዳል ስለዚህ ብዙውን አመራር አፍሩ አገልግሎቱ አደራው ከፍተኛ መሆኑን በማስገንዘብ ከሚሪ የሚጠበቁ ክህሎቶችን ከመጸሐፍ ቅዱስ ካሉ መንፈሳዊ መሪዎች ትምህርት በመጥቀስ ሀሳቦችን በስፋት አስተምረዋል ።
ከዛም በተጨማሪ የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ጥሩ ጅምሮች አሉ በሥርዓተ ትምህርቱ የተጀመረው መልካም ስራን አመስግነው በጠረፋማ ሀገረ ስብከት ያለው የሰንበት ት/ቤት አገልግሎት ልብሰ ስብሐት እንኳን የሌላቸው መኖራቸውን ገልጸው አገልግሎቱ ከዚህም ወጥታችሁ ለሌሎች ወንድም እና እህቶቻችሁ ያላችሁን በማካፈል እና በመደጋገፍ መሆን እንዳለበት ገልጸዋል ።
ቀጣዩ መርሐግብር በወጣት ኤርሚያስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የቴክኖሎጂ ትስስር ማስተባበርያ ኃላፊ ከዚህቀደም የሰንበት ት/ቤቶችን የመረጃ አያያዝ የአቴንዳንስ እና የድረገጽ አገልግሎት የሚሰጥ ሲስተም መጀመሩን አውስተው ያ ሲስተም ለሁለተኛ ጊዜ አገልግሎትን ለማፋጠን ወደላቀ ደረጃ መበልጸጉን አሳውቀው ከዛም በተጨማሪ የሰንበት ት/ቤት አባላት የሚጠቀሙበት የሞባይል ሱፐር አፕ መዘጋጀቱን ለዚህ ጉባኤ ስጦታችን ነው ይህ አፕልኬሽን የጎግል ፕሌይ እስቶር ላይ መጫኑን እና ከቀድሞ ዳታ ቤዝ ሲስተም ጋር የተገናኘ እና የሰንበት ት/ቤት አባላት ይህን አፕልኬሽን በመጠቀም የሁሉንም ሰንበት ት/ቤቶች አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ አስገንዝቧል የሞባይል መተግበሪያውም ብጹእ አቡነ ጢሞጤዎስ ባርከው አስጀምረውታል።ከዛም በማስከተል አባታዊ መመርያ የሰጡሲሆን ዛሬ እኔ እዚህ የተገኘሁት በብጹዕ አቡነቀለሚንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ እና የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀጳጳስ አሳሳቢነት እሳቸውን ወክዬነው አሰቸኳይ ስራ ገጥሟቸው መገኘት አለመቻላቸውን በአካል እዛ ቢሆኑም በሀሳብ ከእኛ ጋር መሆናቸውን ጠቅስው የብጹዕነታቸውን መልእክት አስተላልፈዋል።
በመጨረሻም ለዚህ መዋቅር ትግበራ ከፍተኛ አስተዋጽአ ያደረጉ ሰንበት ት/ቤቶች፣ ክፍለከተማ አንድነተቶች አሰልጣኞች እና የመዋቅር ትግበራ እና የስልጠና አብይ ኮሚቴዎች በብጹእ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቡራኬ እና የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን።
ብጹእነታቸውም ቤተክርስትያን የሁላችንም ነች ኃላፊነቱ የእኛ ብቻ ሳይሆን በየተዋረዱ እናንተም ሀላፊነት አለባችሁ መበርታት ያስፈልጋል ክፍተቶች እንኳን ቢኖሩ በመመካከር በመወያየት መፍታት እንጂ ገበናውን ለአደባባይ ማውጣት ቤተክርስትያንን በመዶሻ እንደማፍረስ ነው ስለዚህ ወጣቱን የምትመሩ እንደመሆናችሁ በሰንበት ት/ቤት የውስጥ ፣የአጥቢያ ይሁን የየትኛውም አካል ችግሮችን በሰከነ እና በኃላፊነት መንፈስ የማንም ደጋፊም ነቃፊም ባለመሆን በጸሎት እና በውይይት እግዚአብሔርን አስቀድመን ቤተክርስትያነንን እንድንጠብቅ አባታዊ መመርያእና አደራ ለጉባኤው አስተላልፈው ጉባኤው በጸሎት ዘግተዋል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት
