የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከማኅበረ ቅዱሳን ወሊሶ ማዕከል ጋር በመተባበር በአፋን ኦሮሞ የሚያገለግሉ 15 ተተኪ መምህራንን አስመረቀ
ኢኦተቤ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ
ግንቦት ፱/፳፻፲፰ ዓ/ም
ዛሬ የተመረቁት ተተኪ መምህራን ለ3 ወራት ግብረ ዲቁና ፣ኪዳን ፣ ሊጦን ፣ መስተበቁዕ ፣ መልክዓ ሥዕል ፣ መልክዓ ቁርባን ፣ መልክዓ ውዳሴ ፣ መልክዓ ማርያም ፣ መልከዓ ኢየሱስ በአፋን ኦሮሞ እንዲሁም ነገረ ሃይማኖት፣ የቤተክርስቲያን ታሪክ ፣ የስብከት ዘዴ ፣ ሐዋርያዊ ተልዕኮ ፣ ነገረ ቅዱሳን ክርስቲያናዊ ሥነ-ምግባር እና ሥርዓተ ቤተክርስቲያን ኮርሶችን የወሰዱ ናቸው ተብሏል።
በምርቃት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ ሌሎችም ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ተገኝተዋል።
ዘገባው የኢኦተቤክ ቴቪ ነው::
