• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

01610

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2008 ዓ.ም የትንሣኤን በዓል አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

01610

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
•በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
•ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
•የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
•በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
•እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
ሞትንና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሣው፣ የሕይወት ራስና የሁሉ ፈጣሪ የሆነው፣ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !!
‹‹ዓይቴ እንከ ቀኖትከ ሞት፤ ወዓይቴ እንከ መዊዖትከ ሲኦል፤
ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?
ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ?›› /1ቆሮ. 15፡55/፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ሞትና መቃብር የኃጢአትና የበደል ውጤቶች እንጂ የተፈጥሮ ዕድል ፈንታ ሆነው ለሰው የተሰጡ አይደሉም ፡፡
ሰው በራሱ ምርጫ ካልሆነ በቀር የሚሞት ሆኖ እንዳልተፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ሲገልጽ ‹‹እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- ‹‹ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ›› ይላል፤ (ዘፍ.2፡16-17)፡፡
ሔዋንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መሠረት አድርጋ ስትናገር፣ ‹‹እግዚአብሔር እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፣ አትንኩትም›› ብሎናል ብላ አረጋግጣለች፤ (ዘፍ.3፡3)፡፡
ከዚህ አምላካዊ ቃል መረዳት እንደሚቻለው አዳም አትብላ የተባለውን ዛፍ ባይበላ ኖሮ አይሞትም ነበር ማለት ነው፤ ከዚህ አንጻር የሞትና የመቃብር ምንጩ ሕገ ተፈጥሮ ሳይሆን ግብረ ኃጢአት ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
በመሠረቱ ግብረ ኃጢአት የሚመነጨው ለእግዚአብሔር ካለመታዘዝ እንደሆነ ከዚህ መረዳት እንችላለን፤ ምክንያቱም አዳምና

0478

የግብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅና የክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የግብረ ሰላም በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ […]

0444

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው የጸሎተ ሐሙስን በዓል አከበሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት ሐሙስ ሚያዝያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገኘት በካቴድራሉ ለተገኘው በርካታ ምዕመናን አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል፡፡ በአስተላለፉት አባታዊ ትምህርት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ሥርዓተ […]

“ሰሙነ ሕማማት”

“ነሥአ ደዌነ መጾረ ሕማመነ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፣ ሕማማችንን ተሸከመ፣ ስለመተላለፋችን ቆሰለ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን” (ኢሳ. 53÷4-6) በማለት ነቢዩ ኢሳይያስ የተነበየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከፍዳና ከዘለዓለማዊ ሞት ለማዳንና ከዲያብሎስም ቁራኝነት ነፃ ለመውጣት ሲል 13ቱን ሕማማተ መስቀልና ሌሎቹንም ጸዋትወ መከራዎች የተቀበለበት ሳምንት “ሰሙነ ሕማማት” በመባል ይታወቃል፡፡ ትርጓሜውም የመከራ ሳምንት ማለት ነው፡፡ […]

“ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ”

በዐቢይ ጾም ከሚታሰቡት ሳምንታዊ በዓላት መካከል ከትንሣኤ ክርስቶስ አንድ ሳምንት በፊት በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በዓለ ሆሣዕና በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በሌሊቱ ስብሐተ እግዚአብሔር በሊቃውንቱ የሚዘመረው መዝሙር ወእንዘሰሙን በዓለ ፋሲካ …” የሚል ሲሆን በጧቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት በቀሳውስቱና በዲያቆናቱ፣ በንባብና በዜማ የሚቀርቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች እንደሚከተለው ተመዝግበዋል፡፡ ዕብ8÷1-ፍ1 ጴጥ1÷13-24 የሐዋ 8÷26-ፍ መዝ 80÷3 […]

00345

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ለመምህር ጎይቶኦም ያይኑ ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ለመምህር ጎይቶኦም ያይኑ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ለመጋቤ ጥበብ ናሁሠናይ በለጠ የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍልና ለአቶ ገ/ሕይወት አስገዶም የሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ኃላፊ ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በትውውቅ አቀባበሉ መርሐ ግብር ወቅት መልአከ ሰላም […]

“ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም”

በዐቢይ ጾም ወቅት ከሚታሰቡት የሳምንታት በዓላት መካከል ከሆሳዕና በፊት ባለው ዕሑድ  የሚታሰበው ሳምንታዊ በዓል ኒቆዲሞስ ይባላል፡፡ ኒቆዲሞስ ኒቆዲሞስ በመባል የሚታወቀው ሰው በዘመነ ብሉይ ኪዳን ፈሪሳዊና የአይሁድ አለቃ የነበረ ሰው ነው፡፡ (ዮሐ 3÷1) የኢየሩሳሌም ሸንጎ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በከሰሰው ጊዜ ኒቆዲሞስ ስለ ክርስቶስ መሰከረ (ዮሐ 7÷45) መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተሰቀለ ጊዜ ኒቆዲሞስ ለመገነዝ የሚውል መልካም መአዛ […]

0168

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለመምህር ጎይተኦም ያይኔ ለሁለተኛ ጊዜ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

ከመጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም  ጀምሮ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ  ሆነው  በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ለተሾሙት ለመምህር ጎይተኦም ያይኔ፣ ለመጋቤ ጥበብ ናሁሠናይ በለጠ የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል ዋና ክፍል ኃላፊና ለአቶ ገ/ሕይወት አስገዶም የሀገረ ስበከቱ ሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ኃላፊ ብፁዕ አቡነ ዕንጦንስ የአውሮፖ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፣መጋቤ ካህናት ኃይለ ሥላሴ ዘማርያም […]

“በጥቂቱ የታመነ በብዙ ይሾማል”

በመምህር ሣህሉ አድማሱ በዐቢይ ጾም ከሚታሰቡት የሳምንታት በዓላት መካከል በ6ኛው ሳምንት የሚታሰበው በዓል ገብርሔር ይባላል፡፡ በዚህ በዓል ወቅት ማለትም ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በሌሊቱ ስብሐተ እግዚአብሔር (ምስጋና) “ገብርሔር ወገብር ምዕመን ዘበሑድ ምዕመነ ኮንከ ዲበ ብዙህ እስይመከ ባዕ ውስተ ፍስሓሁ ለእግዚእከ” የሚለው ያሬዳዊ መዝሙር በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ይቀርባል፡፡ በጧቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት በዲያቆናትና በቀሳውስት፡ መልእክታት፣ የሐዋርያት ሥራ፣ […]

00159

የቅድሥት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን የነበሩት መምህር ጎይተኦም ያይኑ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተመደቡ!!

ቀደም ሲል በመቀሌ ከሣቴ ብርሃን መንፈሳዊ ኮሌጅና በሰዋሰወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩና በኋላም የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የአስተዳደር ምክትል ዲን በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት መምህር ጎይተኦም ያይኑ ከመጋቢት 26 ቀን 2008 ዓ.ም ጀምሮ ወደ አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በመዛወርና የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን እንዲሠሩ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት