• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

d0137

የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ደብር በልማትና በሰላም መስፈን አርአያነት ያለው ተግባር እያከናወነ መሆኑ ተገለጸ

                                                   “ወርሐዊ የገንዘብ ገቢው በእጥፍ አድጓል” በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በነፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ሥር የሚገኘው የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ደብር በልማት ሥራዎች፣ በመልካም አስተዳደር ተግባርና በሰላም መስፈን ላቅ ያለና አርአያነትን የሚያሳይ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ በደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ቀደም ሲል ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባት የልማት […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ የአባዶ ገነት አምባ ቅዱስ ሚካአል ቤተ ክርስቲያን ጐበኙ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሚአስተዳድራቸው ገዳማት፣ አድባራትና የገጠር አብያተ ክርስቲያናት መካከል በየካ ክፍለ ከተማ የአባዶ ገነት አምባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አንዱ ነው፡፡
የአባዶ ገነት አምባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ በየካ ክፍለ ከተማ በኦሮሚያ ዳሌ በሰላሌ ግዛት ድንበር ላይ የተመሠረተ ሲሆን ከኮተቤ የከተማ መዳረሻ እስከ አባዶ ገነት አምባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ድረስ ከሦስት ኪሎ ሜትር ባላነሰ አጭር ርቀት ላይ ይገኛል፡፡
ቤተ ክርስቲያኑ ከተመሠረተ አስራ አምስት ዓመታትን ያስቆጠረ ሲሆን ነባሩን ቤተ ክርስቲያን በአዲስ ሕንፃ ለመተካት የሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ግንባታ እየተከናወነ የሚገኝ በመሆኑና ቤተ ክርስቲያኑ ከከተማው ወጣ ባለ ገጠራማ አካባቢ ላይ በመሠራቱ አብዛኛውን ጊዜም ምዕመናኑ የማይገኙበት በመሆኑና በቤተ ክርስቲያኑ ዙሪያ የሚገኘው ሰፊ የቤተ ክርስቲያኑ ይዞታ ምን እንደሚመስል በጥልቀት ለመረዳትና ለማወቅ ሲባል የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ከሀገረ ስብከቱ የሰበካ ጉባኤ ዋና ክፍል ኃላፊ ከሆኑት ከሊቀ መዘምራን ብርሃኑ ጌጡ ጋር በመሆን ሐሙስ ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም ከሰዓት በኋላ ከቦታው ድረስ በመሔድ የጉብኝት ሥራ አከናውነዋል፡፡
የአባዶ ገነት አምባ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የይዞታ ቦታ ከ30 ሺህ ካሬ ሜትር ያላነሰ መሆኑን ከቦታው ያገኘናቸው የቤተ ክርስቲያኑ የሰበካ ጉባኤ ምክትል ሊቀ መንበር አቶ ሙሉጌታ አብራርተዋል፡፡ ከቤተ ክርስቲያኑ መቆርቆር በፊት

1

“የምናመልከው አምላክ ከሚነደው እሳት ሊያድነን ይችላል!! ”

                                                           በመምህር ሣህሉ አድማሱ ከኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በፊት ከ605-562 በከለዳውያን ላይ ነግሦ የነበረውና ናቡከደነፆር በመባል የሚጠራው የባቢሎን ንጉሥ ከፍታው 60 ክንድ ወርዱ 6 ክንድ የሆነ የወርቅ ምስል (ጣኦት) በማሠራት በባቢሎን አውራጃ በዱራ ሜዳ ላይ አቁሞ የሀገሩን መኳንንት፣ ሹማምንት፣ አገረ ገዢዎች ሁሉ ለወርቁ ምስል (ጣኦት) እንዲሰግዱና ለምስሉ (ለጣኦቱ) በዓል አከባበር እንዲሰበሰቡ አዘዘ፡፡ (ዳን. 3÷1-4) ናቡከደነፆር ያቆመው […]

0087

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሥራ አመራር አባላት የቦሌ ለሚ አቡነ ተክለሃይማኖትን ቤተ ክርስቲያን ጐበኙ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እና ጠቅላላ የሥራ አመራር አባላት የቦሌ ለሚ አቡነ ተክለሃይማኖት ቤተ ክርስቲያንን ማክሰኞ ታህሳስ 12 ቀን 2008 ዓ.ም ጉብኝተዋል፡፡ሰፈራ ጐሮ እየተባለ ከሚጠራው የከተማ ጠርዝ ጀምሮ ቤተ ክርስቲያኑ እስከተሠራበት ድረስ ከአራት ኪሎ ሜትር ያላነሰ ርቀት ያለው ሲሆን አካባቢው ምእመናን የሌሉበት […]

640

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሠራተኞች ሙሉ መረጃ እንዲላክለት ገዳማትና አድባራት መመሪያ አስተላለፈ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አሠራሩን ዘመናዊና ቀልጣፋ ለማድረግ እየጣረ የሚገኝ ሲሆን በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ገዳማትና አድባራት ያለውን አጠቃላይ የሰው ኃይል በኮምፒዩተራይዝድ ሲስተም (ዳታቤዝ) መዝግቦ ለመያዝ ያመች ዘንድ በገዳማቱና በአድባራቱ የሚገኙትን ሠራተኞች ሙሉ ስማቸውን፣ የሥራ መደባቸውን፣ ዕድሜአቸውን፣ ጾታቸውን፣ የትምህርት ደረጃቸውን(በመንፈሳዊና በዘመናዊ) የአገልግሎት ዘመናቸውን፣ የሚከፈላቸውን ወርሐዊ ደመወዝ ጭምር በመግለጽ የተሻለ መረጃ […]

000340

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከጋምቤላ ክልል 21 ወጣቶች ለትምህርት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ያመጣ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጋምቤላ ክልል ከሚገኙት ከላሬ፣ ከኢታንግ፣ ከመኳያ ወረዳዎችና በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው ከፈጋግ ወረዳ የተውጣጡ    1.ሆሶ ታንግ ጋርዌች        11. ጋሉዋክ ቢኖል ዶጥ  2.ሩድ ቱት ኪየር            12. ቡክ ቶንግይክ ጐር3.ሳይመን ቲየል ፑክ       13.ሯች ኒያል ሬጉ4.ጋርዌች ኮንግ ዲየው      14. ያዲክ ቱት ኪር5.ቦሰ ጐት ራንላይ          15. ጅዱ ሬሰ ቾክ 6.ኮንግ […]

የቅዱስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የምስጋና ደብዳቤ አስተላለፈ!!

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር ኮሌጁን ወደ ዩኒቨርሲቲ ለማሳደግ በማሰብ እያስገነባው ለሚገኘው ታሪካዊ፣ ዘመናዊና ሁለገብ ግዙፍ ሕንፃ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ የብር 6,000,000.00 (ስድስት ሚሊዮን ብር) ክፍያ እንዲፈጸም ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የተላለፈውን መመሪያ ተግባራዊ  በመሆኑ ታህሳስ 7 ቀን 2008 ዓ.ም ኮሌጁ ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ምስጋና ያቀረበ ሲሆን በአጠቃላይ ከሀገረ […]

የታቦት ክብር በመጽሐፍ ቅዱስ

ታቦት፡- ቃሉ ግእዝ ነው፡፡ ቤተ = አደረ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ታቦት ማለት የእግዚአብሔር ማደሪያ ማለት ነው ታቦት የጽላቱ ማደሪያ ሲሆን ጽላቱም አሠርቱ ቃላትን የያዘ የእግዚአብሔር ስም የተጻፈበት ስለሆነ ለስሙ መስገድ ይገባል ይህንንም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ጉልበት ሁሉ ለክርስቶስ ስም ይስገድ” ሲል ተናግሯል፡፡ /ፊልጵ2÷10/ ለታቦት መስገድ እንደሚገባ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ማስረጃ አለ ይኸውም “ ኢያሱና የእስራኤልም […]

0896

የስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት!!

0896

ቀድሞ በነቢያት፣ ኋላም በሐዋርያት የተሰበከውና የተገለጠው የቤተ ክርስቲያን የጀርባ አጥንት በመሆን የእግዚአብሔርን ሕገ መንግሥት ሲያስፋፋ የቆየው ስብከተ ወንጌል ሲወርድና ሲዋረድ በመምጣት እኛ ባለንበት ዘመን መድረሱ ይታወቃል፡፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከተመሠረተችበት ጊዜ ጀምሮ የስብከተ ወንጌልን አገልግሎት ከደጋ እስከ ቆላ ስታዳርስ ቆይታለች፡፡
አሁንም ይህንኑ የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ተግባርን አጠናክራ ቀጥላለች፡፡ የተለያዩ ብሔር ብሔረሰቦች መገኛ በሆነው በርዕሰ መዲናችን በአዲስ አበባ ከተማ የሚታየው የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በእጅጉ የሚደነቅ ነው፡፡
የምንመገበው ምግብ፣ የምንለብሰው ልብስ፣ የምንጠለልበት መጠለያ የስብከተ ወንጌል ምርት መሆኑ አይዘነጋም፡፡ ይህ ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል አገልግሎት ከመቼውም በተሻለ ተጠናክሮ ይቀጥል ዘንድ ኅዳር 15 ቀን 2008 ዓ.ም ሊቀማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ከአዲስ አበባ ከተማ አድባራትና ገዳማት ለተገኙ በርካታ የስብከተ ወንጌል ሠራተኞች የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ ዋና ክፍል ኃላፊ መልአከ ሰላም ዳዊት ያሬድ በሰጡት ማብራሪያ የሚከተሉት ቀጣይ የዕቅድ ተግባራት እንደሚከተለው ተዘርዝረዋል፡፡
መደበኛ ሰባክያነ ወንጌልን በሀገረ ስብከቱ አይቲ እና ዶክመንቴሽን ክፍል በኩል ከነፕሮፋይላቸው መዝግቦ መያዝ፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ በስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ ዙሪያ ያሉትን ችግሮች ለይቶ ማወቅና ለችግሮቹ መፍትሔ መስጠት፣ ስለ ዘወትር የስብከተ ወንጌል አገልግሎት እና ዓበይት በዓላት እንዲሁም ልዩ የስብከተ ወንጌል መርሐ ግብሮች በተመለከተ ወጥ መመሪያ ማዘጋጀት፣ በነጻ አገልግሎት እንሰጣለን ስለሚሉ ሰባክያንና ዘማርያን በተመለከተ በማዕከል ፈቃድ ተሰጥቷቸው በሀገረ ስብከቱ በኩል ተረጋግጦ ካልሆነ በስተቀር ከመደበኛ አገልጋዮች ውጭ እንዳያገለግሉ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይቶችን በማካሄድ ጥብቅ መመሪያ ማስተላለፍ፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት የሚገኙትን ሰባክያን ስፖንሰር በማፈላለግ ወይም ከሀገረ ስብከቱ በጀት በማስፈቀድ ወቅታዊና አስፈላጊ በሆኑ ነጥቦች ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ እና የእውቀት ማበልጸጊያ ሥልጠናዎችን መስጠት፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ደረጃ ያሉትን ሰባክያን የአገልግሎት ዘመናቸውን እና ያሳዩትን የሥራ ፍሬ በመገምገምና በመለካት ወደተሻለ የሥራ ኃላፊነት ቦታ ላይ እድገት ተሰጥቷቸው እንዲሠሩ ማድረግ፣ ቋሚ የሆነ በ3 ወር አንድ ጊዜ የሰባክያነ ወንጌል አጠቃላይ ስብሰባ እንዲኖር ማድረግ፣ በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ከሥራ ኃላፊዎች ጋር ስለ ስብከተ ወንጌል እንቅስቃሴ በሰፊው በመወያየት ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲሰጡ ማድረግ፣ በየጊዜው በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ስለሚካሄዱ ጉባዔዎች ከክፍለ ከተማ የስብከተ ወንጌል ኃላፊዎች ጋር በመሆን በየአብያተ ክርስቲያናቱ በመገኘት ቁጥጥር ማድረግ፣ በዓመቱ ውስጥ በአጠቃላይ በሁሉም ክ/ከተሞች የስብከተ ወንጌል ቀን እንዲኖር ማድረግ፣ የልምድ ልውውጦችን ማካሔድ፣ ስለአንድነት ጉባዔው ጠቃሚነት ስለአጋጠሙ

5ቱ ስጦታዎች እና ሥርዓታቸው

                                                                                                                                     ከመጋቤ አእላፍ ፋሲል ታደሰ (ቀሲስ)
ሥርዓተ አምልኮ  ከሚገለጥበት መንገድ አንዱ ስጦታ ነው፡፡ የሰው ልጅ ከራሱ  የሆነ አንዳች የለውም  በጎ የሆነውን ሁሉ ከፈጣሪ ዓለማት  ከእግዚአብሔር ያገኘው  ነው፡፡ በመሆኑም ፈጣሪያችን መስጠትን  እንዳስተማረን ሁሉ እኛም ተገዥነታችንን ከምንገልጥበት  አንዱ ከእርሱ የተቀበልነውን በፈቃደኝነት በደስታ በመስጠት ነው፡፡ ነቢዩ ዳዊት ይህን ሲያሰረዳ “ሁሉ ከአንተ ዘንድ ነውና ከእጅህ  የተቀበልነውን ሰጥተንሃልና ይህን ያህል ልናቀርብልህ የቻልን ማነን?… በፈቃዴ ይህን አቅርቤአለሁ” በማለት ከእግዚአብሔር  ያገኘውን ሀብት በደስታ  በፈቃዱ ለቤተ መቅደስ ሥራ እንዲውል መስጠቱን በመግለጽ ስለ ስጦታ ጽፏል/1ኛ. ዜና!9. 9-06/:: ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ  “ ነገር ግን ሁሉ በአግባብና በሥርዓት ይሁን” በማለት እንዳስተማረን ለእግዚአብሔር የምንሰጠው የአምልኮት መግለጫ በሥርዓት ልናደርገው እና ከልብ  ሊሆን ይገባል፡፡ ለዚህ  ደግሞ መሠረቱ የስጦታ ዓይነቶችንና የአቀራረብ ሥርዓቱን ማወቅ ነው፡፡ በዚህች አጭር ጽሑፍም በሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን መሠረት መንፈሳዊ ምግባራት የሆኑትን አምስቱ የስጦታ ዓይነቶች ምጽዋት፣መባዕ፣ሰእለት፣ በኩራት እና አሥራትን እንመለከታለን፡፡
1. ምጽዋት፡-
ምጽዋት መስጠት ከገንዘብ፣ ከዕውቀት፣ከንብረት…ከመሳሰሉት ላይ ለእግዚአብሔር ቤት እና ለችግሮኞች መለገስ ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ  በአንቀጸ ብፁዓን ትምህርቱ “ ብፁዓን መሐርያን፣ የሚምሩ ብፁዓን” ናቸው ያለውስ ለምጽዋት ሲሆን ሊቃውንት ሲተረጉሙት በሦስት መንገድ ያስቀምጡታል፡፡ እነዚህም፡-
ሀ/ምሕረት ሥጋዊ፡- ይህ የሚያስረዳው ለሥጋ የሚሆን ነገርን መለገስን ሲሆን በይበልጥ ለችግረኞች በማሰብ ለኑሮ የሚያስፈልጋቸውን ነግሮች መለገስን ያመለክታል፡፡
ለ/ምሕረት መንፈሳዊ፡- በምክር ፣ በትምህርት… በሥነ ልቡናን የሚያንጽ /የሚያበረታ/ መንፈሳዊ

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት