የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከጋምቤላ ክልል 21 ወጣቶች ለትምህርት ወደ አዲስ አበባ ከተማ ያመጣ መሆኑ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በጋምቤላ ክልል ከሚገኙት ከላሬ፣ ከኢታንግ፣ ከመኳያ ወረዳዎችና በደቡብ ሱዳን ከሚገኘው ከፈጋግ ወረዳ የተውጣጡ
1.ሆሶ ታንግ ጋርዌች 11. ጋሉዋክ ቢኖል ዶጥ
2.ሩድ ቱት ኪየር 12. ቡክ ቶንግይክ ጐር
3.ሳይመን ቲየል ፑክ 13.ሯች ኒያል ሬጉ
4.ጋርዌች ኮንግ ዲየው 14. ያዲክ ቱት ኪር
5.ቦሰ ጐት ራንላይ 15. ጅዱ ሬሰ ቾክ
6.ኮንግ ፑድ ዋንግ 16. ጓሄር ጋዴድ ጋል
7.ቾል ዶት ኔን 17. ቾል ቦስ ሉዋክ
8.ሙድ ፓክ ሆል 18. ላም ቾል ሉዋን
9.ቾል ጆክ ሆል 19. ኒያል ኛንግ
10.ፈም ኮንግ ደንግ 20. ጋምቤላ ሩወይ ዲየው
21.ጋድቤል ላም የተባሉ ወጣቶችን የብሔር ብሔረ ሰቦዎችን በዓል ለማክበር ጋምቤላ ከተማ የተገኙት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ እሁድ ታህሣሥ 3 ቀን 2008 ዓ.ም ከጋምቤላ ይዘው በመምጣት አዲስ አበባ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል በተገነባው የአብነት ት/ቤት አስገብተዋቸዋል፡፡
ከላይ በስም የተገለፁት የጋምቤላ ክልል ማህበረ ሰከ ወጣቶች መካከል አራቱ በሰላሳዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን አስራ ሰባቱ ወጣቶች ግን በአስራዎችና በሃያዎች የዕድሜ ክልል ሥር ይገኛሉ፡፡
ከሃያ አንዱ ወጣቶች መካከል አንዱ ወጣት በደቡብ ሱዳን ፈጋግ በተባለው ወረዳ ትዳር መሥርቶ የአራት ልጆች አባት ሲሆን ለዚህ የትምህርት ዕድል መምጣት የቻለው በትዳር ጓደኛውና በወላጅ እናቱ መልካም ፈቃድ መሆኑን ግለሰቡ አስረድቷል፡፡ ለትምህርት ወደ አዲስ አበባ በመምጣቱ በቤተሰቦቹ ላይ የኢኮኖሚ ጫና እንደማይፈጠር ጨምሮ ገልጾልናል፡፡ ወጣቶቹ የሚማሩአቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ታሪክ፣ ሥርዓተ ቤተክርስቲያን፣ ትምህርተ ሃይማኖት፣ የአሰባበክ ዘዴና ሥርዓተ ቅዳሴ በዋናነት ይጠቅሳሉ÷ ወጣቶቹ በአዲስ አበባ ከተማ ለሦስት ተከታታይ ዓመታት ይቆያሉ፡፡ ከሦስት ተከታታይ ቆይታ በኋላ ወደ ክልላቸው ተመልሰው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አምባሳደሮች /ልዑካን/ በመሆን ስብከተ ወንጌልን በማስፋፋት አገልግሎት ይሰጣሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አለኝታና መጠጊያ የሆነው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በቀጣዩ መርሐ ግብር ይህን ዓይነቱን የተቀደሰ ተግባር አጠናክሮ እንደሚቀጥልበትና ሕዝበ ክርስቲያኑም ከሀገረ ስብከቱ ጐን በመሰለፍ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲአደርግ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ በሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ካቴድራል ተገኝተው ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ ታህሣሥ 10 ቀን 2008 ዓ.ም በሰዓሊተ መሕረት ካቴድራል ተገኝተው ሥርተ ቅዳሴው እንደተጠናቀቀ ከበርካታ ምዕመን ፊት በመቆም ወደ ክርስትና እምነት በመምጣታችን ደስ ብሎናል፣ በአንድ አምላክ እናምናልን የሚል መዝሙር በኑዋርኛ ቋንቋ ዘምረዋል ከምዕመናንም በጭብጨባ የታገዘ ከፍተኛ የሞራል ድጋፍ አግኝተዋል፡፡
{flike}{plusone}
