• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

“ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት ናት” በማለት ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ገለጹ

ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት መሆኗን የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ በመልእክታቸው ገለጹ። ቤተክርስቲያን የክርስቲያኖች የኅብረት ቤት ናት፤ በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነት አንድ የሆኑ ሁሉ የሚጠመቁባት፣ የክርስቶስን ሥጋውንና ደሙን የሚቀበሉባት በመጨረሻም በሰላም የሚያርፉባት ናት በማለት አብራርተዋል። ብፁዕነታቸው ይህንን መልእክት ያስተላለፉት ግንቦት 7 ቀን 2013 ዓ/ም በየካ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ስር በሚገኘው […]

“ከአሁን በኋላ ከውጪ ሆናችሁ ሳይሆን ከውስጥ ሆናችሁ አስቀድሱ” ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ

የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ “ከአሁን በኋላ ከውጪ ሆናችሁ ሳይሆን ከውስጥ ሆናችሁ አስቀድሱ” በማለት መልእክት አስተላለፉ። ብፁዕነታቸው መልእክቱን ያስተላለፉት በቀን 6/09/2013 ዓ.ም አዲስ ተገንብቶ የተጠናቀቀውን የኮልፌ ደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያንን በጸሎት ከባረኩ በኋላ ነው። ግዙፍ የሆነው ይህ ሕንጻ ቤተክርስቲያን በጸሎት ስለተባረከ ከአሁን በኋላ በውጪ ቆማችሁ አታስቀድሱ፣ እንደመቃኞው […]

መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች

የተለያዩ መሠረታዊ የኮምፒውተር ደህንነት መጠበቂያ መንገዶች አሉ፡፡ከእነዚህ ውስጥ ሁሉም ሰው የጥቃት ዒላማ ውስጥ መሆኑን መረዳትና ለዚህ ሁልጊዜም ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ነው፡፡ለሶፍትዌሮች ወቅታዊና የዘመኑ ሶፍትዌሮችን መጫንም የኮምፒውተሮችን ደህንነት መጠበቂያ መሠረታዊ መንገድ መሆኑ ይነገራል፡፡በተጨማሪም ቀጥተኛ የደህንነት ዝመና በየጊዜው የሚያቀርቡ እንደ ክሮም ወይም ፋየር ፎክስ ያሉ የድረ-ገጽ ማፈላለጊያዎችን መጠቀም ፣እንደ ፍላሽ፣ ሀርድ ዲስክ እና የመሳሰሉ ተንቀሳቃሽ መሣሪያዎችን ሲጠቀሙ […]

በዚህ ዘመን ለመብል የሚሞት ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያን ትንሣኤ የሚሞት አባት/ጳጳስ ያስፈልጋል ተባለ

የ2013 ዓ/ም የጌታችን ትንሣኤ በዓልን ምክንያት በማድረግ የብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የእንኳን አደረሶት ዝግጅት በሀገረ ስብከቱ በድምቀት ተከብሮ ውሏል። በዝግጅቱ የተገኙት በሰሜን አመሪካ የካልፎርንያ አከባቢ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቴዎፍሎስ ትምህርት ሰጥተዋል። ጌታችን “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ፥ ትወደኛለህን? ብሎ ጴጥሮስን ሲጠይቀው “አዎን ጌታ ሆይ እንድወድህ አንተ ታውቃለህ” ሲለው “ጠቦቶቼን ጠብቅ፣ በጎቼን አሰማራ” የሚል ትልቅ ሐላፊነት አሸከሞታል […]

በቦሌ ደ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍት በድምቀት ተከበረ

ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ የአዲስ አበባና የጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት በቦሌ ደ/ገ/ቅ/ጊዮርጊስ እና ቅ/ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን የቅዱስ ጊዮርግስ በዓለ ዕረፍት በድምቀት ተከብሯል። የ2013 የቅዱስ ጊዮርጊስ በዓለ ዕረፍቱ ሚያዚያ 23 በሕማማት ውስጥ የዋለ በመሆኑ ክብረ በዓሉ ተሻግሮ ዛሬ ሚያዚያ 27/2013 ዓ/ም ተከብሮ ውሏል። በዕለቱ በመጋቤ ሐዲስ ቆሞስ አባ ኒቆዲሞስ የቅድስት ሥላሴ ካቴድራ የመጽሐፍ መምህር ትምህርት […]

የትንሣኤን በዓል አስመልክተው ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ያስተላለፉት መልእክት

“ተንሥአ በከመ ይቤ” (ማቴ ፳፰፥፮)እንደ ተናገረ ተነሥቶአል (ማቴ 28፥6) ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱና ዋነኛው የትንሣኤ በዓል ነው። ትንሣኤ “ተንሥአ” ከሚለው የግዕዝ ግስ የተወሰደ ሲሆን ትርጉሙም መነሣትን ያመለክታል፤ ከሞት በኋላ በነፍስ ብቻ ሳይሆን በሥጋም ጭምር ሕያው ሆኖ መነሣትን የሚገልጽ ቃል ነው። “ኃጢአተኞችን ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ […]

የኢየሱስ ክርስቶስን የስቅለት በዓል አስመልክተው ብፁዕ አቡነ መልከጼዴቅ ያስተላለፉት መልእክት

ፍጹም ፍቅር ጊዜው ከዛሬ 2000 ዓ.ም ገዳማ በፊት ነበር ዕለቱ ደግሞ ዕለተ አርብ ። ለዘመናት በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ዕንቅፋት ሆኖ የቆየው የኃጢአት ግድግዳ የፈራረሰበትና በአንጻሩ ደግሞ ጽኑ የምሕረትና የጽድቅ ድልድይ የተገነባበት፣ በሥልጣን ላይ የነበረው ሞት በጊዜ ገደብ ምክንያት ሥልጣኑን ለሕይወት ያስረከበበት፣ ዓመተ ፍዳም ከአቅም ማነስ የተነሣ መንበረ መንግሰሥቱን ለመሪው ለዓመተ ምህረት የለቀቀበት ክስተቶች የተከናወኑበት ዕለት […]

“በሞቱ ከመሰልነውም: በትንሳኤው እንመስለዋለን” ሮሜ. 6:5

ለአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ፅ/ ቤት ሰራተኞች፣ ለገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ለሁሉም ምእመናን በያላችሁበት መልካም ሰሙነ ህማማት( የፀሎት፣ ስግደት እና የቅዱሳት መፃህፍት የንባብ ጊዜ) ይህንላችሁ:: ትንሳኤውን ለማየት በህማማቱ በኩል ማለፍ/ መሳተፍ እንደሚገባ ሲያመለክት ቅዱስ ጳውሎስ “ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከሞት፣ ትንሳኤውን በሚመስል ትንሳኤ ከእርሱ ጋር እንነሳለን” ያለውን ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያናችን ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ታደርገዋለች: […]

የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ የሕማማትና የትንሣኤ በዓላትን አስመልክቶ መመሪያ አስተላለፉ!!

ሚያዚያ 14 ቀን 2013 ዓ.ም የአዲስ አበባና ጉራጌ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምሮ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ መ/ር አካለወልድ ተሰማና ልዩ ልዩ የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት በሀገረ ስብከቱ የስብሰባ አዳራሽ የሰሙነ ሕማማትና የትንሣኤ በዓላት አከባበር መንፈሳዊ ይዘቱን ጠብቆ እንዲከበር አባታዊ መመሪያ አስተላልፈዋል፡፡ከሆሳእና ጀምሮ ያሉት የሕማማትና የትንሣኤ በዓላት ልዩ ልዩና በርካታ መንፈሳዊ ሥርዓቶች የሚፈጸሙባቸው በዓላት በመሆናቸው […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት