• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ።

የአዲስ አበባ ከተማ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 12ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ተካሄደ። በመርሐ ግብሩ ላይ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት የቦርድ ሰብሳቢ የተለያዩ የሃይማኖት ተቋማት አባቶች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዋና አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ሙዚና ከድር፣ ከፍተኛ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሥራ ሐላፊዎች፣ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤትን ለመመርመር በጠቅላይ ቤተ ክህነት የተቋቋመውን አጥኚ ኮሚቴ አስመልክቶ የተሰጠ መግለጫ።

መስከረም 10 ቀን 2017 ዓ.ም በቁጥር 782/354/2017 ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት ለአጣሪ ኮሚቴ በአድራሻ ሲጻፍ በተመዘገበልን ግልባጭ ለመገንዘብ እንደቻልነው በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሚስተዋሉ የአመራር ግድፈቶችንና በአሠራር ላይ እየተፈጠሩ ያሉ ችግሮችን አጥንቶ የሚያቀርብ ኮሚቴ መቋቋሙን ተረድተናል፡፡ ለኮሚቴው መቋቋም ምክንያቱ “በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት የሚስተዋሉ የአሰራር ግድፈቶች ላይ የተፈጠሩ ችግሮች ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሱ […]

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ የመስቀል ደመራ በዓል ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ መከበሩን አስመልክቶ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሀገረ ስብከቱ የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል ፍጹም ሰላማዊ በሆነ ሁኔታ በመከበሩ የምስጋና መልእክት አስተላለፈ። የ፳፻፲፯ ዓ/ም የመስቀል ደመራ በዓል በመስቀል ዐደባባይ ቅዱስ ፓትርያርካችን፣ ክብርት የኢፌዴሪ ፕሬዚደንት፤ ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሚኒስትሮች፣ የአሜሪካን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት አምባሳደሮች በመቶ ሺ የሚቆጠሩ ምዕመናን በተገኙበት […]

ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል በከፍተኛ ድምቀትና ሰላም መከበሩን አስመልክቶ የምስጋና መልዕክት አስተላለፈች።

የ፳፻ ፲ወ፯ ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል በታላቅ ሃይማኖታዊ ሥነሥርዓትና ድምቀት ተከብሮ በመዋሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የተሰማትን ደስታ ትገልጻለች። በዓሉ በተዋበና በደመቀ መልኩ ተከብሮ መዋል ይችል ዘንድ ሕዝበ ክርስቲያኑ ዝናብና ቁር ሳይበግረው በጽናትና ፍጹም በሆነ መንፈሳዊነት በዓሉን ማክበሩ እጆግ የሚያስደንቅ ሲሆን መርሐ ግብሩ በተቀመጠለት ጊዜ ገደብ መጠናቀቅ እንዲችል ተረኛው ደብር፣ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ልጆቻችንና በበዓሉ […]

“#የመስቀሉ ቃል ማለት እግዚአብሔርን ፍሩ፣ ለእርሱም ታዘዙና ተገዙ ማለት ነው” ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! “እስመ ነገረ መስቀሉሰ ዕበድ ውእቱ በኀበ ኅጉላን ወበኀቤነሰ ለእለ ድኅነ ኃይለ እግዚአብሔር ውእቱ፤ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት ነው፤ ለኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው”(1ቆሮ. 1÷08)፤ በመስቀሉ ኃይል ከፍዳ ኃጢአት ያዳነን ጌታችን አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት በዓለ ቅዱስ መስቀል በሰላም አደረሰን […]

የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የማጠቃለያ የምክክር ጉባኤ ተካሔደ።

የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል አከባበርን አስመልክቶ የማጠቃለያ የውይይት ጉባኤ ተከናወነ። በየዓመቱ የሚከበረው የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል ቤተ ክርስቲያናችን በዐደባባይ ከምታከብራቸው ከጌታ ዘጠኙ ንዑሳን በዓላት መካከል አንዱ ነው። የ፳፻፲፯ ዓ/ም የሚከበረው የቅዱስ መስቀል ደመራ በዓል አስመልክቶ በዚህ ወር በተለያዩ ቦታዎችና ደረጃዎች የውይይት መድረኮች ተዘጋጅተው ሲከናወኑ ቆይተዋል። በዛሬው ዕለት የእነዚህ ውይይቶች ማጠቃለያ መርሐ ግብር ብፁዕ አቡነ ሄኖክ […]

የቤተክርስቲያን ተወካዮች በግብፁ ጉባኤ ላይ ያልተገኙት በግል በገጠማቸው እክል ምክንያት መሆኑን የውጭ ግንኙነቱ መምሪያ አስታወቀ።

መስከረም 6 እና 7/2017 ዓመተ ምሕረት በግብፅ አል ናትሩ አባ ቢሾይ ገዳም በኮፕቲክ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አስተናጋጅነት በተካሄደው የአኃት እና የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ያልተገኙት በግል በገጠማቸው እክል ምክንያት ሲሆን ተተኪ ልዑክ ለመላክ እስከ መስከረም 3 ቀን 2017 ዓመተ ምሕረት ድረስ የተደረገው ጥረት ቪዛን ጨምሮ […]

የሊቀ መላእክት ቅዱስ ራጉኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በመርካቶ ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ድምቀት ተከብሯል።

በበዓሉን ለማክበር ብፁዕ አቡነ ማርቆስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን የስብክተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ሊቀ ጳጳስ፣ ብፁዕ አቡነ በርናባስ የዋግኽምራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የገዳማትና የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ምእመናንና ምእመናት ተገኝተዋል።@ተሚማ

“ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ እና ለሁለንተናዊ ለውጥ ራስን ማዘጋጀት ይኖርብናል”። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ሊቀ ጳጳስ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ” የዘመናት ባለቤት እግዚአ ሰማያት ወምድር ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለ 2017 ዘመነ ማቴዎስ የምሕረት ዓመት በሰላምና በጤና አደረሰን አደረሳችሁ” በማለት የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። በመልእክታቸውም:- ” አዲስ ዓመት፤ የዓመታት፣ የወራት፣የሳምንታት እና የቀናት ለውጥና መፈራረቅ ብቻ ሳይሆን ካለፈው ዓመት ስህተት ወደ አዲሱ ዓመት እንዳይሸጋገር ማድረግ […]

“በዓሉን ስናከብር በጦርነት እና በልዩ ልዩ ምክንያቶች በችግር ውስጥ የሚገኙ ወገኖቻችንን በማሰብ እውነተኛ የክርስቶስ ተከታዮች መሆናችንን ልናረጋግጥ ይገባል”… ብፁዕ አቡነ ሄኖክ

ብፁዕ አቡነ ሄኖክ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስና የተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል የበላይ ጠባቂ የ2015 ዓ.ም በዓለ ልደትን አስመልክተው የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል። የመልእክቱ ሙሉ ቃል እንደሚከተለው ይቀርባል። “ዮም በርህ ሠረቀ ለነ ሰማይ ወምድር ዘኢያገምሮ ማኅፀነ ድንግል ፆሮ “(ዛሬ ብርሃን ወጣልን ፤ ሰማይ እና ምድር መሸከም የማይችሉትን የድንግል ማኅፀን ተሸከመው “(ቅዱስ ያሬድ) በመላው ዓለም የምትገኙ […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት