የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በአዲስ አበባ የሰላምና የያብሮነት የጸሎት መርሐ ግብር ” ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን ለዘላቂ ሰላማችን ” በሚል መሪ ቃል ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት እና የሌሎች ሃይማኖት ተቋማት ተወካዮች በተገኙበት አደረገ
ግንቦት 16 /2018 ዓ/ም
በአራዳ ፓርክ በተከናወነው ጸሎት መርሐ ግብሩ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፤አገኘሁ ተሻገር የፌዴሬሽን ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ፣ ንቡረዕድ ኤልያስ አብርሃ የጠቅላይ ቤተክህነት የመንፈሳዊ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ : መልአከ ምሕረት ቆሞስ አባ ገብረ መድኅን ንጉሤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች የየገዳማት አስተዳዳሪዎች እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል።
በሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተዘጋጀው ሀገር አቀፍ ልዩ የጸሎት መርሐ ግብር ላይ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ባደረጉት ንግግር ዘጠና ስምንት በመቶ አማኝ ህዝብ ያለበ ሀገር ዎች እንደመሆኑ መጠን የሃይማኖት መሪዎች ለሀገር ሰላም በአብሮነት መቆም አስፈላጊ በመሆኑ በአንድነት ለሀገር ሰላም ልንጸልይ ይገባል ብለዋል ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቃነጳጳስ ፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያው ሓላፊዎች እና የአድባራት አስተዳዳሪዎች የመሐረነ አብ ጽሎት ያደረሱ ሲሆን በብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ቃለምዕዳን እና ቡራኬ ተሰጥቷል።
©EOTC TV
