“አፍሪካ መጠበቅ አትችልም” በሚል ርዕስ ፤ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን አህጉር አቀፍ የአየር ንብረት ዘመቻ በይፋ አስጀመረች ።
ጳጉሜን ፬/፳፻፲፰ ዓ/ም አ/አ/ሀገረ ስብከት ሚዲያ
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድዖ ኮሚሽን፣ ከ’ACT Alliance’
እና በአየር ንብረት ላይ በትብብር ከሚሠሩ የአፍሪካ የእምነት ተቋማትና አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር “አፍሪካ መጠበቅ አትችልም ከቃል ኪዳን ወደ ፍትሐዊ ትግበራ” (Africa Can’t Wait: From Pledges to Just Implementation) የተሰኘ የአየር ንብረት ዘመቻን በይፋ አስጀመረች።
ይህ ዘመቻ አዲስ አበባ ላይ ከሚካሄደው የኮፕ32 (COP32) ጉባኤ አስቀድሞ፣ በመላው አፍሪካ ጠንካራ የፓን-አፍሪካ የአየር
ንብረት እንቅስቃሴ ለመገንባት እና የአየር ንብረት ቃል ኪዳኖች በፍትሃዊነትና በሰብአዊ መብት ላይ በተመሠረተ መልኩ እንዲተገበሩ ለመጠየቅ አንድ ሚሊዮን ፊርማዎችን ለማሰባሰብ ያለመ ነው።
ከ14ኛው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥና ልማት ጉባኤ (CCDA-XIV) ጎን ለጎን በተካሄደውና ከመላው አፍሪካ የመጡ ከ100 በላይ ተሳታፊዎች በተገኙበት በዚህ መርሐ ግብር ላይ፤ የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ የቤተክርስቲያኒቱን አቋም የሚያንጸባርቅ ሰፋ ያለ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።
በመክፈቻ ንግግራቸው ላይ ለእኛ ለእምነት ተከታዮች፣ ለፍጥረት እንክብካቤ ማድረግ የአካባቢ ጥበቃ ኃላፊነት ብቻ አይደለም። መንፈሳዊ እና ሞራላዊ ጥሪ ጭምር ነው። መጽሐፍ ቅዱስ በኦሪት ዘፍጥረት 2፥15 ላይ የሰው ልጅ ኤደን ገነትን እንዲያለማትና እንዲጠብቃት እንደተቀመጠ ያስታውሰናል። ስለዚህ ምድርን የመጠበቅ እና ለመጪው ትውልድ የማቆየት ኃላፊነት የተሰጠን የእግዚአብሔር ፍጥረት ጠባቂዎች (stewards) ነን በማለት ገልፀዋል።
አክለውም ጠባቂነት ሁልጊዜም ከፍትሕ ጋር አብሮ መጓዝ አለበት። በትንቢተ ኢሳይያስ 1፥17 ላይ፣ ቅዱስ ቃሉ “መልካም ማድረግን ተማሩ፥ ፍርድን [ፍትሕን] ፈልጉ፥ የተገፋውንም አድኑ” በማለት ጥሪ ያቀርብልናል። ይህ ዛሬ ላለው የአየር ንብረት ፍትሕ ኃይለኛ መልእክት ነው። ፍትሕን መፈለግ ማለት፣ ለአየር ንብረት ቀውሱ አነስተኛ አስተዋጽኦ አድርገው ነገር ግን እጅግ የከፋ መዘዝ እየደረሰባቸው ያሉትን ማኅበረሰቦች ማዳመጥ እና ከጎናቸው መቆም ማለት ነው። ይህም የአየር ንብረት ፋይናንስ፣ ማላመድ (adaptation)፣ ጉዳት እና ኪሳራ (loss and damage)፣ መልሶ ማቋቋም እና ወደ ንጹሕ ኃይል የሚደረገው ሽግግር የሰውን ልጅ ክብር የሚያስጠብቅ እና ይበልጥ ለሚፈልጉት የሚደርስ መሆኑን ማረጋገጥ ማለት ነው በማለት ገልጸዋል ።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለትውልዶች የዘለቀ የጠባቂነት (stewardship) ትውፊት አላት። የተቀደሱ የቤተ ክርስቲያን ደኖቻችን (አድባራትና ገዳማት ደኖች) እምነት፣ መንፈሳዊነት እና ለፍጥረት የሚደረግ እንክብካቤ አብረው ሊጓዙ
እንደሚችሉ ሕያው ምስክሮች ናቸው። ፍጥረትን መጠበቅ ለአፍሪካ አዲስ ኃላፊነት እንዳልሆነ፤ በታሪካችን፣ በባህላችን እና በእሴቶቻችን ውስጥ ጠልቆ የገባ መሆኑን ያስታውሱናል በማለት ተናግረዋል።
ፕሮፌሰር አባ ኃይለ ገብርኤል ግርማ በንግግራቸው ወደ ፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ ያመጣናል። የአየር ንብረት ለውጥ የሀገር ድንበሮችን፣ የእምነት ተቋማትን ወይም የሃይማኖት ወጎችን አያከብርም። የእኛም ምላሽ በእነዚህ ሊከፋፈል አይገባም። የፓን-አፍሪካኒዝም መንፈስ፣ አፍሪካ ጠንካራ የምትሆነው ሕዝቦቿ በአንድ የጋራ ዓላማ ዙሪያ አብረው ሲቆሙ መሆኑን ያስታውሰናል በማለት ተናግረዋል ።
የሲ.ሲ.አር.ዲ.ኤ (CCRDA) ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ በበኩላቸው ሕዝባችን ቀድሞውንም ከተለዋዋጭ የአየር ንብረት መዘዞች ጋር እየኖሩ ባሉበት በዚህ ወቅት አፍሪካ ሌላ አዋጅ መጠበቅ አትችልም። ድርቅ ሰብልን ሲያጠፋ፣ ጎርፍ ቤትን ሲያፈርስ፣ የመሬት መራቆት የኑሮ መሰረትን ሲያናጋ፣ እና ቤተሰቦች ለትውልድ መኖሪያቸው ብለው ከጠሩት ቦታ ሲፈናቀሉ አፍሪካ መጠበቅ አትችልም። ወጣቶች እነሱ ያልወሰኑትን ውሳኔ መዘዝ ብቻ ሳይሆን እነሱ ያልፈጠሩትን ሥርዓት የመጠገን ሸክም ሲወርሱ አፍሪካ መጠበቅ አትችልም በማለት ተናግረዋል።
አፍሪካ መጠበቅ አትችልም ነገር ግን አፍሪካ መምራት ትችላለች። እናም አፍሪካ መምራት እንዳለባት አምናለሁ። በቁጣ ብቻ አይደለም። በጥገኝነት አይደለም። ዓለም ተጋላጭነታችንን እንዲገነዘብ በመጠየቅ ብቻ አይደለም። እኛ በሞራል ልዕልና፣ በአፍሪካዊ ጥበብ፣ በሳይንሳዊ እውቀት፣ በእምነት፣ በፈጠራ፣ በአንድነት እና በተግባራዊ መፍትሄዎች መምራት አለብን በማለት ገልጸዋል።የእምነት ማኅበረሰቡ በተለይ ጠቃሚ ሚና ያለው እዚህ ላይ ነው ብዬ አምናለሁ ። አማኙ ሕዝባችን የአፍሪካ የልማት ታሪክ ተመልካቾች አይደሉም። እኛ የታሪኩ አካል ነን። በመንደሮች ውስጥ እንገኛለን። በከተሞች ውስጥ እንገኛለን። በአርሶ አደሮች፣ በሴቶች፣ በወጣቶች፣ በተፈናቀሉ ማኅበረሰቦች እና በችግሩ ግንባር ቀደም ተጋላጭ በሆኑ ቤተሰቦች መሐል እንገኛለን በማለት ተናግረዋል።
ዶ/ር ንጉሡ ለገሠ በንግግራቸው ሰዎችን በደስታቸው ጊዜ ብቻ ሳይሆን በመከራቸው ጊዜም አብረናቸው እንሆናለን። ስለዚህ፣ ስለ አየር ንብረት ፍትህ ስንነጋገር፣ ከተልዕኳችን ውጭ ስለሆነ ጉዳይ እየተነጋገርን አይደለም። እየተነጋገርን ያለነው ስለ ጥሪያችን/ተልዕኳችን ነው። የዚህ ዘመቻ ርዕስ ላይ “ፍትሕ” የሚለውን ቃል የተቀበልኩትም ለዚህ ነው። ምክንያቱም የአየር ንብረት ቀውሱ ስለ ሙቀት መጠን፣ ልቀት እና ካርቦን ብቻ አይደለም። ከእያንዳንዱ ስታስቲክስ ጀርባ የሰው ሕይወት አለ። ከእያንዳንዱ ድርቅ ጀርባ ቤተሰብ አለ። ከእያንዳንዱ ጎርፍ ጀርባ ማኅበረሰብ አለ። ከእያንዳንዱ የተፈናቀለ ቤተሰብ ጀርባ ታሪክ አለ። እናም ከእያንዳንዱ የጠፋ የኑሮ መሰረት ጀርባ የፍትህ ጥያቄ አለ። አየሩ የጋራችን ነው። ውቅያኖሶቹ የጋራ ናቸው። የመሬት እና የውሃ ስርዓቶች የተሳሰሩ ናቸው። የልጆቻችንም የወደፊት እጣ ፈንታ የጋራ ነው። ስለዚህ፣ ኃላፊነታችንም የጋራ መሆን አለበት በማለት ገልጸዋል ።
#EOTCTV
See less
May be an image of dais and text that says ‘INTERFAITH VOICES INTERFAITHVOICESFOR FOR T CLIMATE ACTION UR R R U ERS R E 45 ドドナい WHHOVOCACY AOVOCACY ۱ي VOCAC MEASRICA まう’. May be an image of crowd and text. May be an image of text that says ‘Atr Ca Va 1’. May be an image of one or more people, dais and text. No photo description available.
Shared p
