• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

346

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

346

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ ትንሣኤሁ ለእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡
– በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
– ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
– የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
– በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
– እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
በሞትና በመቃብር ላይ ሥልጣን ያለው ኃያሉና አሸናፊው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
‹‹ወበከመ በእንተ አዳም ኵልነ ንመውት ከማሁ በክርስቶስ ኵልነ ነሐዩ፤ ሁላችን በአዳም እንደምንሞት እንደዚሁም ሁላችን በክርስቶስ ሕያዋን እንሆናለን›› (1ቆሮ. 15÷22)፡፡
እዚህ ላይ በተገለፀው ቃለ እግዚአብሔር መሠረት የሰዎች መጻኢና የመጨረሻ ዕድል ከሁለት አዳማዊ ውርስ ጋር የተያያዘ ሆኖ ይገኛል ፡፡
በቅዱስ መጽሐፍ በግልጽ እንደተጻፈው ሰው ሁሉ ከቀዳማዊ አዳም በሥጋ ተወልዶአል፤ የእርሱ የሆነውንም ሁሉ ወርሶአል፤ይህም ማለት በሥጋው በኩል የግብረ ኃጢአት ዝንባሌን፣ ሞተ ሥጋን፣ ወሪደ መቃብርን፣ በመቃብር ውስጥ መበስበስንና መፍረስን ሲወርስ በነፍሱ በኩል ደግሞ ከእግዚአብሔር መለየትን፣ በኃጢአት ተሸንፎ የዲያብሎስ ሎሌ መሆንን፣ በኃጢአቱ ምክንያት ለኵነኔ ሲኦል ተጋላጭ መሆንን እና የመሳሰሉትን ሁሉ ወርሶአል ማለት ነው፡፡
ጠቅለል አድርገን ስናየው ቀዳማዊ አዳም በሥጋና በነፍስ ከባድ ውድቀትን ለልጆቹ አውርሶአል ማለት ነው ፡፡
ከቀዳማዊ አዳም የውድቀት ዘመን ጀምሮ

00030

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የ2007 ዓ.ም. የትንሣኤ በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ሊ/ማ/ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የአ/ አ/ ሀ/ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡እንኳን ለ2007 ዓ.ም የጌታችን፤የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤው መታሰቢያ በዓል ሁላችንንም ጠብቆ አደረሰን አደረሳችሁ በማለት በራሴና በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስም መልካም ምኞቴን እገልፃለሁ፡፡ የጌታችን ትንሣኤ የሰው ልጆች ሁሉ ከሞት ወደ ሕይወት የተሸጋገሩበት በመሆኑ የሁሉም የሰው […]

233

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከግብፁ ፕሬዚዳንት ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ

የሕዳሴ ግድብን መሠረት በማድረግ የስምምነት ፊርማ ሱዳን ላይ አድርገው ለይፋዊ ጉብኝት ወደ ሀገራችን የመጡትና ከሀገራችን ከፍተኛ መሪዎች ጋር ተገናኝተው ስለ አጠቃላይ የጋራ እሴቶችና የጋር ጥቅሞች አብሮ ተባብሮ ማሳደግ ስለሚቻልበት ሁኔታ እጅግ መልካም በሆነ ሁኔታ ሲነጋገሩና ስምምነት ላይ የደረሱትን የግብፁ ፕሬዚዳንት ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ […]

ጾምን ለዩ ምህላውንም በዚህ ቀን ይሁን ብላችሁ አዋጅ ንገሩ ፣አለቆችንም ሰብስቧቸው፤ ከፈጣሪችን ከእግዚአብሔር ማደሪያ የሚኖረውንም ሰ ብ ስ ቡ ት ፣ ሁላችሁም አንድነት ሆናችሁ ወደ እግዚአብሔር ለምኑ፡፡ ኢዩ 2÷15

ሙሉ የኆኀተ ጥበብ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሔትን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ (‹‹የመጋቢት 2007 ዓ.ም ኆኀተ ጥበብ ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሔት››)

00030

የአ/አ/ሀ/ስ/ ዋና ስራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈ ስቅዱስ ከሀገረ ስብከቱና ከክፍለ ከተማ ሠራተኞች ጋር በጋራ ሥራ ለመሥራት በሚያስችል ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄዱ

በዓይነቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ሊባል በሚችል ሁኔታ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም በሀገረ ስብከቱና እንዲሁም በገዳማትና አድባራት ልብሰ  ተክህኖ በለበሱ ካህናትና ልዩ ልዩ ሠራተኞች እጅግ በጣም ደማቅ አቀባበል የተደረገላቸው የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈ ስቅዱስ ከ2 ቀናት በኋላ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከ7ቱም ክፍላተ ከተማ መላው ሠራተኞች ጋር መጋቢት 18/2007 ዓ.ም በሀገረ […]

0010

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት ካህናት አዲስ ለተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቀባበል አደረጉ!!!

በመናገሻ  ገነተ ጽጌ  ቅ/ጊዮርጊስ ቤ/ክ  በዋና ጸሐፊነት ሲያገለግሉ የነበሩት ሊቀ ማእምራን የማነ ብርሃን ዘመንፈሰ ቅዱስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና  በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ  የሊቃውንት ጉባኤ አባል በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት መጋቤ ብሉይ  አእመረ አሸብር  ምክትል ሥራ አስኪያጅ በመሆን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ተመድበዋል፡፡  አዲስ የተመደቡት ዋና ሥራ አስኪያጅና ምክትል ሥራ አስኪያጁ  ዛሬ መጋቢት 16/2007 ዓ.ም  ከጠዋቱ […]

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር ለሚገኙ ገዳማትና አድባራት አዲስ ለሚቀጠሩ የአብነት መምህራን ውድድር ተካሄደ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በሥሩ ለሚገኙ አድባራትና ገዳማት የአብነት መምህራንን አወዳድሮ ለመቅጠር ባወጣው መርሐ ግብር መሰረት ፈተናውን ያለፉ መምህራን 32 መሆናቸው ተገጸ፡፡በሀገረ ስብከቱ የትምህርት ክፍል ዋና ክፍል ኃላፊ ሊቀ ማዕምራን ብርሃነ መስቀል ገበየሁን ጠይቀን እንደተረዳነው እነዚህ መምህራን በድጓ፣ በቅዳሴ ፣ በአቋቋም፣ በቅኔ፣ በዝማሬ መዋሥዕት፣ በብሉያት እና በሐዲሳት ተወዳድረው የተሻለ ውጤት በማምጣታቸው ነው ያለፉት በማለት ተናግረዋል፡፡አያይዘውም […]

0019

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖ 2ኛ ዓመት በዓለ ሲመት ተከበረ

የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 2ኛ ዓመት የፕትርክና በዓለ ሲመት በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የካቲት 24 ቀን 2007 ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፤ የሃይማኖት መሪዎች፤ የመንግሥት ባለ ሥልጣናት፤ አምባሳደሮች፤ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የየመምሪያ ኃላፊዎች፤ የድርጅት ኃላፊዎች፤ የኮሌጅ ኃላፊዎች፤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፤ […]

0005

በመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ተካሄደ

የካቲት 14 እና 15 2007 ዓ.ም ብፁአን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና ሊቃውንት ቤተ ክርስቲያን በተገኙበት በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ  ልዕኮ ዋና ክፍል አስተባባሪነት የአንድነት ጉባኤው ተጀምሯል፡፡ በዚሁ የአንድነት ጉባኤ መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ መምህራን ወቅቱን አስመልክተው ለምዕመናን ትምህርተ ወንጌል የሰጡ ሲሆን እንደዚሁም ወቅቱን የተመለከቱ የተለያዩ  መዝሙሮች በተለያዩ ዘማሪያን ቀርበዋል፡፡በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ስብከተ […]

በኢ/ኦ/ተ/ቤ/ ክ/መ/ፓ/ጠ/ፅ/ቤት የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የአዲስ አድማስ ጋዜጣ አዘጋጆች የቤተክርስቲያኒቱን ስም ከማጥፋት እንዲታቀቡ አሳሰበ

አዲስ አድማስ ጋዜጣ የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤት ወጣቶች የፓትርያሪኩን እገዳ ተቃወሙ በሚል ርዕስ ቅዳሜ የካቲት 14/2007 ዓ.ም በቅጽ 14 ቁጥር 788 በጋዜጣው ፊት ለፊት ላይ አሳትሞ የቤተክርስቲያኒቱን ስም ማጥፋቱ አይዘነጋም፡፡ ይህንን ተከትሎም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለሰንበት ትምህረት ቤቶች ማደራጃ በቁጥር 3092/546/07 በቀን፡- 19/06/07 ዓ.ም በፃፈው ደብዳቤ የካቲት 8 ቀን 2007 ዓ.ም ሀገረ ስብከቱ ከሰንበት […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት