• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

0544

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለሁለተኛ ዙር ያሰለጠናቸውን የገዳማትና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች በሠርተፍኬት አስመረቀ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት ከገዳማቱና አድባራቱ ለተውጣጡ ቁጥራቸው 30 ለሆነ የሒሳብ ሠራተኞች ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር፤ የቋሚና የአላቂ ንብረት አያያዝና አወጋገድን አስመልክቶ ለ3 ወራት ያህል የሰለጠኑ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተገኙበት ሰኞ ጥር 16 ቀን 2008 ዓ.ም በሰርተፍኬት አስመርቋል፡፡ሰልጣኞቹ በመማር ማስተማር ሂደቱ ላይ ባደረጉት ንቁ ተሳትፎ በሀገረ ስብከቱ በኩል ተሻላሚ ሲሆኑ የሰልጣኞችን […]

9090

የ2008 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በድምቀት ተከበረ !!!

የጌታችን የመድኃኒታቺን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ዘንድ በመላ ሀገሪቱ ተከብሮ ውሏል።በዓሉ ኢየሱስ ክርስቶስ  በዮሃንስ እጅ ለመጠመቅ ወደ ባህረ ዮርዳኖስ የወረደበትን ዕለት ለማሰብ  የሚከበር ነው፡፡በተለይም በዓሉ በአዲስ አበባ ጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት በድምቀት በተከበረበት ወቅት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን  ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም […]

የአቃቂ ቃሊቲ የጥምቀት ባህር ቦታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ይዞታ ሆኖ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጽ/ቤት ፈቃድ ሰጠ

የአቃቂ ቃሊቲ የጥምቀተ ባህር ቦታ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፖትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖትና በክቡር አቶ ደሪባ ኩማ የአዲስ አበባ ከተማ ዋና ከንቲባ የጋራ ምክክርና ውይይት በኋላ 25ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው የጥምቀተ ባህር ቦታ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ይዞታ ሆኖ እንዲቀጥል […]

0018

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ የ2008 ዓ.ም በዓለ ጥምቀትን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!ከሁሉ በማስቀደም የሁላችንም አስገኚና የሕይወት ምንጭ እግዚአብሔር አምላካችን በሕይወትና በጤና ጠብቆ ለብዓለ ልደቱና ጥምቀቱ ስላደረሰን ምስጋና ይግባው፡፡ አምካችን እግዚአብሔር ከዘመን መለወጫ የቅዱስ ዮሐንስ በዓል እስከ ልደቱና ጥምቀቱ ድረስ በሰጠን ጊዜ በርካታ ነገሮችን አከናውኖልናል፡፡ የጀመርነውን የሒሳብ አሠራር ለውጥ ለማስፋት ሁለተኛ ዙር የሒሣብ ሠራተኞች ሥልጠና በተሳካ ሁኔታ ያጠናቀቅነው ባለፈው አጭር […]

በዓለ ቅድስት ሥላሴ

ሥላሴ የሚለው ቃል ‹‹ሠለሰ›› ሦስት አደረገ ከሚለው የግዕዝ ሥርወ ቃል የተገኝ ሲሆን ይህም ሦስትነት ማለት ነው፡፡ ምሥጢረ ሥላሴ ብለን ስለነገረ ሃይማኖት ስንናነገር ግን አንድም ሦስትም ተብሎ ይተረጎማል፡፡ በዚህም መሠረት እግዚአብሔርን አንድም ሦስትም ብለን ማመናችንን የምንገልፅበት የሃይማኖት ዶግማ ነው፡፡እንደሚታወቀው የሥላሴ አንድነት ስንል በባህርይ በህልውና በፈቃድ…. አንድ አምላክ ማለታችን ሲሆን  ሦስትነት ስንል ደግሞ በስም’ በአካል’ በግብር ነው፡፡የሥላሴ […]

0178

የአዲስ አበባ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና ከካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ጋር በመተባበር በሰላም ዙሪያ ለአንድ ቀን የቆየ የምክክር ጉባኤ አካሄደ

የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትና በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ከፍትሕና ሰላም ቢሮ ጋር በመተባበር ቁጥራቸው 150 ለሚደርሱ ከሰባት ቤተ እምነት ለተውጣጡ የሃይማኖት አባቶች ማክሰኞ ታህሳስ 3 ቀን 2008 ዓ.ም በግዮን ሆቴል ዘላቂና ማኅበራዊ ሰላምን ለማረጋገጥ የሚያስችል የአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ወርክሾፕ አድርጓል፡፡ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም መለሰ የጠቅላይ […]

01750

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ተወካዮች ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የእንኳን አደረስዎ መልእክት አስተላለፉ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት ተወካዮች ቅዳሜ ታህሳስ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ጀምሮ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ በመገኘት ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘንበረ ተክለሃይማኖት የእንኳን አደረስዎ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በእንኳን አደረስዎ […]

640

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በ2ኛው ዙር የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ለጠናቀቁ የሒሳብ ባለሙያዎች አዲሱን አሠራር በተመለከተ የሥራ መመሪያ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ለዘመናት ሲሠራበት የነበረውን የሲንግል ኢንትሪ ሒሰብ አሠራር ወደ ደብል ኢንትሪ ዘመናዊ የሒሳብ አሠራር መቀየሩን ተከትሎ በሥሩ ለሚገኙ ገዳማት እና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች የሙያ ማሻሻያ (የአቅም ግንባታ)ሥልጠና እየሰጠ መሆኑን ተከትሎ በመጀመሪያው ዙር 30 የሒሳብ ባለሙያዎችን አሰልጥኖ ማስመረቁ እና ተመራቂዎቹም በተመደቡባቸው አብያተ ክርስቲያናት ሥራ መጀመራቸው ይታወቃል፡፡ በዚህም ረቡዕ ታኅሣሥ 27 ቀን 2008 ዓ.ም […]

01610

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት የ2008 ዓ.ም የልደት በዓልን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ  ዘተናገረ በእንተ በዓለ ልደት  ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐትበስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን->በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣->ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤->የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤->በሕመም ምክንያት በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤->እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤የርስተ መንግሥቱ ወራሾች እንሆን ዘንድ […]

ሰላም በምድር

                                “ሰላም በምድር”የዓለም መድኃኒትና የሰላም አለቃ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደበት ሌሊት ሰማያውያን ሠራዊትና ምድራውያን ሰዎች በአንድ ላይ የዘመሩት መዝሙር “ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ወሰላም በምድር ሥምረቱ ለሰብእ” የሚል ነው፡፡ ይህም የምሥራች ቃል ትርጓሜው “ምስጋና ለእግዚአብሔር በሰማያት፣ ሰላምም በምድር ለሰውም በጎ ፈቃድ ይሁን” ማለት ነው፡፡ (ሉቃ. 2÷14)፡፡ ይህ ቃል የሰላምን አስፈላጊነት አጉልቶ የሚያሳይ ሲሆን በአንፃሩ ደግሞ ሰላም […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት