• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

“የቤትህ ቅናት አቃጠለኝ”

በመምህር ሣህሉ አድማሱ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ አስተምሕሮ መሠረት በጾመ ኢየሱስ (ዐቢይ ጾም) ከሚከበሩት የሳምንታት በዓላት መካከል ሦስተኛው ሳምንት “ምኩራብ” በመባል ይታወቃል፡፡ የበዓሉ መታሰቢያ የሚታሰበው በዋናነት በዕለተ እሁድ ሲሆን በዚህ ዕለት በሌሊቱ ማሕሌታዊ ሥርዓት ወቅት “ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ…” የሚል የቅዱስ ያሬድ ድርሰት በሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን በዜማ ይቀርባል፡፡ በሥርዓተ ቅዳሴው ወቅት ደግሞ ቆላ. […]

0062

የጣሊያን ሪፐፕሊክ ፕሬዝዳንት ሰርጊዮ ማታሬላ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ

የተከበሩ ሚስተር ሰርጊዮ ማታሬላ የጣሊያን ሪፐፕሊክ ፕሬዝዳንት ሰኞ መጋቢት 5 ቀን 2008 ዓ.ም በመንበረ ፓትርያርክ ተገኝተው ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ጋር በአካባቢ ጥበቃ፣ በስደተኞች ጉዳይ እና በጋራ መልካም ግንኙነት ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡ ፕሬዝደንቱ ከብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር ውይይት ባደረጉበት ወቅት በ20ዎቹ ዓመታት ውስጥ የተደረገው […]

g0021

የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የልማት እንቅስቃሴ

የምሥራቀ ፀሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ቤተክህነት ሥር የሚገኝ ሲሆን ይህ ቤ/ክ በ1986 ዓ.ም በአካባቢው ምዕመናን ተመሠረተ፡፡ የቤተክርስቲያኑ የይዞታ ቦታ 79,571 ካሬ ሜትር ስፋት አለው ሲሆን በቤተክርስቲያኑ በልዩ ልዩ የሥራ መስክ የተመደቡ ሠራተኞች ብዛት 93 ናቸው፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ እየተሠሩ የሚገኙ የልማት ሥራዎች በ3,310 ካሬ ሜትር ስፋት ላይ ያረፈ ሕንጻ ቤተክርስቲያን ግንባታ፤ለአስራ […]

640

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በታሪኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ለሰባክያነ ወንጌል ፈተና ሰጠ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከተ በስሩ ላሉት ገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ለመመደብ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈተና ሰጠ፡፡ ሀገረ ስብከቱ የመግቢያ ፈተናውን ያዘጋጀው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት የሊቃውንት ጉባኤና ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን በተውጣጡ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ለፈተናው ከተመዘገቡት አመልካቾች መካከልም በትምህርት ማስረጃቸው የተመረጡ 64 እጩዎች ለፈተና ተቀምጠዋል፡፡ በፈተናውም በዘመናዊ ትምህርት እስከ ማስተርስ ዲግሪ በመንፈሳዊም የአብነት ትምህርት ምሥክር የሆኑ […]

አሥሩ ማዕረጋት

በመጋቢ አእላፍ ቀሲስ ፋሲል ታደሰ የቀበና ም/ፀሐይ መድኃኒዓለም ቤ/ክ/ስ/ወ/ኃላፊ ማዕረግ ማለት ክብር፣ ሥልጣን ማለት ነው፡፡ ቅዱሳን በገድልና በትሩፋት ብዛት የሚያገኟቸውን ዐሥር ማዕረጋትና ከዐሥር ቁጥር ጋር ያላቸውን ተያያዥነት እንመለከታለን፡፡ ቁጥር ምንድን ነው? በዕብራይስጥ ብዛትን ሲገልጥ ቁጥር በፊደል እንጂ በአኃዝ ምልክት ብዙ ጊዜ አልተጻፈም፡፡ በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ ቁጥር አጠቃቀም ሌላ ነገር አለ፤ ይኸውም ቁጥሮች አንዳንድ ጊዜ የነገር፣ […]

w00822

ቅዱስ ሲኖዶስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባለ 4 ነጥብ መግለጫ አወጣ

                           የካቲት 29 ቀን 2008 ዓ.ም.በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ፡፡ከኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫኅሡ ሰላማ ለብሔር እስመ በሰላመ ዚአሃ ይከውን ሰላምክሙ(የአገርን ሰላም ሹ ፈልጉ የአገራችሁ ሰላም የእናንተ ሰላም ነውና)የተወደዳችሁ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት !የሐገርና የወገን ፍቅር ያለው ሕዝብ ሰላም ከእግዚአብሔር መሆኑን ያውቃል፣ ሰላም ለሰው ልጆች ከማናቸውም መሠረታውያን ፍላጎቶች በላይ ተቀዳሚ ጉዳይ […]

የቦሌ ክፍለ ከተማ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት የ2008 ዓ.ም የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት አቀረበ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትጋር  በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተው መርሐ ግብሩን በጸሎት ከጀመሩ በኋላ የደብረ ጽጌ ቅዱስ ኡራኤል ቤተ ክርስቲያን ሊቃውንት፣ አንሰ አፋቀርኩ ጵጵስናከ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ፣ ትክበር ነፍስየ በቅድመኰሎሙ ሊቃነ ጳጳሳት ወካህናት ትብል ደብረ ጽጌ፡፡የሚለውን […]

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2008 ዓ.ም ዐቢይ ጾምን አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

ቃለ በረከት ዘብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዘተናገረ በእንተ በዓተ ጾም ዓቢይ ዘእግዚእነ ወአምላክነ ወመድኃኒነ ኢየሱስ ክርስቶስ ሎቱ ስብሐት፡፡
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ በተለያዩ ክፍላተ ዓለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ሕዝበ ክርስቲያን በሙሉ፤
ምሕረቱ የበዛ መዓቱ የራቀ ቸርና ሰው ወዳጅ የሆነው እግዚአብሔር አምላካችን እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት የጌታችን፣ የአምላካችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መዋዕለ ጾም ዓቢይ በሰላም አደረሳችሁ !!
‹‹ወአንሰ መጻእኩ ከመ ይርከቡ ሕይወተ ወፈድፋደ ይርከቡ፣ እኔ የተትረፈረፈ ሕይወት እንዲያገኙ መጣሁ›› (ዮሐ10፡10)
ይህ ቃል የሕይወት አስገኚና ሰጪ የሆነው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለሰው ልጆች ዘላቂና ዘላለማዊ ሕይወት ሊሰጥ ሰው ሆኖ ወደሰዎች እንደመጣ ሲያመለክት የተናገረው ቃለ አድኅኖ ነው ፡፡
ለፍጡራን ሁሉ ትልቁና የመጀመሪያው ጸጋ ሕይወት ነው፤ ሰውም ሆነ ሌሎች ፍጥረታት በዚህ ዓለም ሲወጡና ሲወርዱ የሚገኙት ሕይወትን ለመንከባከብ፣ ለመጠበቅና ለማስቀጠል ነው፤
ምክንያቱም ሕይወት ካለ በሕይወት መሣሪያነት ሁሉም ይገኛል፤ ሕይወት ከሌለ ግን ሁሉም የለምና ነው ፡፡
በመሆኑም ሕይወት በፍጡራን ዘንድ ተወዳዳሪና መተኪያ የሌላት ሀብት ናትና ሙሉ ጥበቃና እንክብካቤ ሊደረግላት ይገባል ፤
አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋችንንና ነፍሳችንን በመዋሐድ ፍጹም አምላክ፣ ፍጹም ሰው ሆኖ በዓለም ላይ የተገለጠው ሕይወታችንን ለመጠበቅ፣ ለመንከባከብና ለማዳን ነው ፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ተገልጦ ይመላለስ በነበረበት ጊዜ ሕይወትን አጥተው በጉስቁልና የነበሩ የተለያዩ ሕሙማን ሕይወተ ሥጋን እንዲያገኙ አድርጎአል፤
ሕይወተ ነፍስን አጥተው የነበሩትም በሕያው ትምህርቱ ተስፋ ሕይወትን እንዲላበሱ አድርጎአል፤ ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ሙታን ሕይወታቸውን ተጎናጽፈው ከመቃብር እንዲነሡ አድርጎአል፤ በእነዚህ ሁሉ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሕይወት ራስ መሆኑን ከመግለጽ ጋር ለሰው ልጆች ሁሉ ሕይወትን ለመስጠት እንደመጣ በትምህርትም በተግባርም አሳይቶአል ፡፡
ከዚህ አንጻር ሕይወት በፈጣሪም ሆነ በፍጡራን ምን ያህል ታላቅ ዋጋ እንዳላት

ሥርዓተ ጸሎት በኢ.ኦ.ተ.ቤተ ክርስቲያን

                                                             ሥርዓተ ጸሎትጸሎት፡-ቃሉ ግእዝ ነው ጸለየ ለመነ ከሚለው ግሥ የወጣ ሲሆን ጸሎት፡- ማለት ልመና  ነው፡ጸሎት ምስጋናም ነው ‹‹ይትቀደስ ስምከ›› (ስምህ ይቀደስ) ስንል ምስጋና ነው ‹‹ሲሳየነ ዘለለእለትነ ሀበነ ዮም›› (የእለት ምግባችንን ስጠን ዛሬ) ስንል ደግሞ ልመና  ነው፡፡ እንዲሁም ጸሎት፡- ሰው ከልዑል እግዚአብሔር ጋር የሚነጋገርበት ነው፡፡ (ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ 14) በምን አይነት መንገድ መጸለይ እንዳለብን ከዚህ እንደሚከተለው […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት