• "እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና" መዝ 135:1

  • ”ባህርም አይታ ሸሸች : ዮርዳኖስም ወደ ኋላው ተመለሰ : ተራሮች እንደ ኮርማዎች ዘለሉ” መዝ 113 ፥ 3

0602

የኢትዮጵያና የሱዳን የሕዝብ ለሕዝብ የሰላም ግንባታና የጋራ ጥቅም ግንኙነት የልዑካን ቡድን ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ ጋር ውይይት አደረገ

በማኅበራዊና ሃይማኖታዊ ዕሴቶች ዙሪያ የሕዝቦች ለሕዝቦች ሀገራዊ ግንኙነትን ለማበለፀግ  ሲንቀሳቀስ የቆየው ሱዳናዊ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን በሰላም ግንባታና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሠረተውን ባህል አጠናክሮ ለመቀጠል ይቻል ዘንድ ቅዳሜ ግንቦት 6 ቀን 2008 ዓ.ም  በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር በሚገኘው በምሳካዬ ኅዙናን ገዳም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተወካዮች ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አካሂዷል፡፡ ይህ ታላቅ ሀገራዊ […]

pp002

የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል የ2008 ዓ.ም የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለበርካታ ችግሮች ታላቅ የምሳ ግብዣ አደረገላቸው!!

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኘው የመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል እሑድ ሚያዚያ 30 ቀን 2008 ዓ.ም ቁጥራቸው ከ1,000 በላይ ለሚሆኑ ነዳያን /ችግረኞች ሰፊ የሆነ የምሳ ግብዣ ያደረገላቸው መሆኑን የዝግጅት ክፍላችን ከቦታው ድረስ በመሄድ አረጋግጧል፡፡ ይህ ታላቅ የምሳ ግብዣ የተከናወነበት ቦታ ቀደም ሲል በነገሥታቱ፣ በመሳፍንቱ፣ በመኳንንቱና በደጅአዝማቾቹ ዘመን በተመሠረተውና 107 ዓመት እድሜ ባስቆጠረው የካቴድራሉ የሰንበቴ […]

0516

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሒሳብ ሠራተኞች የ1ና የ2ኛ ዙር ሥልጣኞች ወደ ተግባር የሚያስገባ ተጨማሪ ሥልጠና እየተሰጣቸው ነው

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና የአድባራት የሒሳብ ሠራተኛች ቀደም ሲል በሀገረ ስብከቱ በተዘጋጀው የሥልጠና ማዕከል ከ2ወራት በላነሰ ሲሰለጥኑ የቆዩ ሲሆን ይህንኑ የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና ወደተግባር የሚያስገባ ለ4 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ የሒሳብ ሥራ ሥልጠና በተጋባዥ ባለሙያዎች እየተሰጣቸው መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ አብዛኞቹ ሠልጣኞች በአካውንቲንግ የመጀመሪያ ድግሪ ያላቸው ሲሆን የተወሰኑት ሠልጣኞች በቲኦሎጂ በዲኘሎማና በድግሪ መርሐ ግብር ተመርቀዋል፡፡ […]

“ሕያዉን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋላችሁ?”ሉቃ. 24፡5

ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን እንደሚነሣ ቅዱሳን ነቢያት አስቀድመው ትንቢት ተናግረዋል፡፡ ከትንቢቶቹም አንዱ “ወተንሥአ እግዚአብሔር ከመ ዘንቃሕ እምንዋም፡፡ ወከመ ኃያል ወኅዳገ ወይን:: ወቀተለ ጸሮ በድኅሬሁ” (የተኛ ሰው ከእንቅልፍ እንደሚነቃ እግዚአብሔር ከሙታን ተነሣ የወይን ስካር እንደተወው እንደ ኃያልም ሰው፤ በኋላው በተተከለ መስቀል ጠላቱን ድል አደረገ) /መዝ. 77፡65/ ስለ ጌታችን ትንሣኤ አራቱም ወንጌላውያን ጽፈዋል፡፡ ይህም /ማቴ. […]

01610

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ የ2008 ዓ.ም የትንሣኤን በዓል አስመልክተው መልእክት አስተላለፉ

01610

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
•በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፣
•ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
•የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
•በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
•እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት፤
ሞትንና መቃብርን ድል አድርጎ የተነሣው፣ የሕይወት ራስና የሁሉ ፈጣሪ የሆነው፣ ጌታችን፣ አምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ስምንት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ !!
‹‹ዓይቴ እንከ ቀኖትከ ሞት፤ ወዓይቴ እንከ መዊዖትከ ሲኦል፤
ሞት ሆይ መውጊያህ የት አለ?
ሲኦል ሆይ ድል መንሣትህ የት አለ?›› /1ቆሮ. 15፡55/፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት
ሞትና መቃብር የኃጢአትና የበደል ውጤቶች እንጂ የተፈጥሮ ዕድል ፈንታ ሆነው ለሰው የተሰጡ አይደሉም ፡፡
ሰው በራሱ ምርጫ ካልሆነ በቀር የሚሞት ሆኖ እንዳልተፈጠረ ቅዱስ መጽሐፍ ሲገልጽ ‹‹እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፡- ‹‹ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤ ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህ›› ይላል፤ (ዘፍ.2፡16-17)፡፡
ሔዋንም የእግዚአብሔርን ትእዛዝ መሠረት አድርጋ ስትናገር፣ ‹‹እግዚአብሔር እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ፣ አትንኩትም›› ብሎናል ብላ አረጋግጣለች፤ (ዘፍ.3፡3)፡፡
ከዚህ አምላካዊ ቃል መረዳት እንደሚቻለው አዳም አትብላ የተባለውን ዛፍ ባይበላ ኖሮ አይሞትም ነበር ማለት ነው፤ ከዚህ አንጻር የሞትና የመቃብር ምንጩ ሕገ ተፈጥሮ ሳይሆን ግብረ ኃጢአት ሆኖ እናገኘዋለን ፡፡
በመሠረቱ ግብረ ኃጢአት የሚመነጨው ለእግዚአብሔር ካለመታዘዝ እንደሆነ ከዚህ መረዳት እንችላለን፤ ምክንያቱም አዳምና

0478

የግብረ ሰላም በዓል በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በድምቀት ተከበረ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጰሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ኃላፊዎች፤የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አስከያጅና የክፍል ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በተገኙበት ቅዳሜ ሚያዝያ 22 ቀን 2008 ዓ.ም የግብረ ሰላም በዓል በታላቅ ድምቀት ተከብሯል፡፡ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ […]

0444

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው የጸሎተ ሐሙስን በዓል አከበሩ

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ተክለሃይማኖት ሐሙስ ሚያዝያ 20 ቀን 2008 ዓ.ም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋር በመገኘት በካቴድራሉ ለተገኘው በርካታ ምዕመናን አባታዊ ትምህርት እና ቃለ ምዕዳን አስተላልፈዋል፡፡ በአስተላለፉት አባታዊ ትምህርት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በጸሎተ ሐሙስ የደቀ መዛሙርቱን እግር በማጠብ ሥርዓተ […]

“ሰሙነ ሕማማት”

“ነሥአ ደዌነ መጾረ ሕማመነ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ፣ ሕማማችንን ተሸከመ፣ ስለመተላለፋችን ቆሰለ፣ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን” (ኢሳ. 53÷4-6) በማለት ነቢዩ ኢሳይያስ የተነበየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከፍዳና ከዘለዓለማዊ ሞት ለማዳንና ከዲያብሎስም ቁራኝነት ነፃ ለመውጣት ሲል 13ቱን ሕማማተ መስቀልና ሌሎቹንም ጸዋትወ መከራዎች የተቀበለበት ሳምንት “ሰሙነ ሕማማት” በመባል ይታወቃል፡፡ ትርጓሜውም የመከራ ሳምንት ማለት ነው፡፡ […]

“ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ”

በዐቢይ ጾም ከሚታሰቡት ሳምንታዊ በዓላት መካከል ከትንሣኤ ክርስቶስ አንድ ሳምንት በፊት በታላቅ ድምቀት የሚከበረው በዓለ ሆሣዕና በመባል ይታወቃል፡፡ በዚህ ዕለት ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ በሌሊቱ ስብሐተ እግዚአብሔር በሊቃውንቱ የሚዘመረው መዝሙር ወእንዘሰሙን በዓለ ፋሲካ …” የሚል ሲሆን በጧቱ ሥርዓተ ቅዳሴ ወቅት በቀሳውስቱና በዲያቆናቱ፣ በንባብና በዜማ የሚቀርቡት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥቅሶች እንደሚከተለው ተመዝግበዋል፡፡ ዕብ8÷1-ፍ1 ጴጥ1÷13-24 የሐዋ 8÷26-ፍ መዝ 80÷3 […]

00345

የአዲስ አበባ ገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ለመምህር ጎይቶኦም ያይኑ ደማቅ አቀባበል አደረጉላቸው

በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሥር የሚገኙ የገዳማትና አድባራት ሰባክያነ ወንጌል ለመምህር ጎይቶኦም ያይኑ የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ለመጋቤ ጥበብ ናሁሠናይ በለጠ የሀገረ ስብከቱ የሰው ኃይል አስተዳደር ዋና ክፍልና ለአቶ ገ/ሕይወት አስገዶም የሀገረ ስብከቱ የሒሳብና በጀት ዋና ክፍል ኃላፊ ሰኞ ሚያዚያ 10 ቀን 2008 ዓ.ም ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል፡፡ በትውውቅ አቀባበሉ መርሐ ግብር ወቅት መልአከ ሰላም […]

ማስታወቂያ

አስተያየቶች

    በፌስቡክ ያግኙን

    © በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት