የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ቡራኬ ቤተ ክርስቲያኑ ተፈጸመ።
መስከረም ፳/ ፳፻፲፱ ዓ.ም አዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ አገልገግሎትየመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ዕድሳት ተጠናቆ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ቡራኬ ቤተ ክርስቲያኑ ተፈጸመ።
ለዕድሳቱ የፈጀው ጊዜ 3 ወር መሆኑን የገለጹት የገዳሙ ዋና አስተዳዳሪ መ/ፀሐይ ቆሞስ አባ ኪዳነማርያም ዮሴፍ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ጸሎትና እገዛ ሳይለያቸው በማኅበረ ካህናቱና ምእመናኑ ትብብር ዕድሳቱ በአጭር ጊዜ መጠናቀቁን ገልጸዋል።
ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊና የራያ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሥራው በአጭር ጊዜ እንዲህ አሸብርቆ ተሠርቶ ማለቁና መባረኩ በእግዚአብሔር ጥበብ የተሠራ መሆን እንደሚያስረዳ ተናግረዋል።
ያለ እግዚአብሔር እርዳታ ምንም ምን ልንሠራ እንደማንችል የገለጹት ብፁዕ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ለዚህ ድንቅ ሥራ እርሱ ስለ ረዳን በአጭር ጊዜ የተከናወነ መሆኑን አምነን በእርሱ ደስ ሊለን እና እርሱን ልናመሰግን ይገባል ብለዋል።
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ እንኳን ለዐዲስ ዓመት እና ብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ ካሉ በኋላ ዕድሳቱ ድንቅ መሆኑን ገልጸው በዕድሳቱ ሥራ ለተሳተፋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይባርካችሁ ይቀድሳችሁ ብለዋል።
ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያኑ ግሩም ድንቅ በሆነ መልኩ በአጭር ጊዜ ዐድሳችሁ ፀሐይ እንዲመስል ያደረጋችሁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ካሉ በኋላ ዘመኑ ዘመነ ሰላም እንዲሆንልን በመመመኘት መርሐ ግብሩን በጸሎተ ቡራኬ ዘግተውታል።
©EOTC TV
የቅዱስነታቸው ጸሎት ቡራኬ አይለየን!
