በዓለ ዕርገት
“ከሰማይም ከወረደ በቀር ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም፥ እርሱም በሰማይ የሚኖረው የሰው ልጅ ነው።”
ዮሐንስ ፫፥፲፫
💠ከጌታችን ዘጠኝ ዐበይት በዓላት መካከል በዓለ ዕርገት አንዱ ነው።
በዓሉ ከትንሣኤ በ፵ኛው ቀን ይከበራል።
“ደግሞ አርባ ቀን እየታያቸው ስለ እግዚአብሔርም መንግሥት ነገር እየነገራቸው፥ በብዙ ማስረጃ ከሕማማቱ በኋላ ሕያው ሆኖ ለእነርሱ ራሱን አሳያቸው።”
ሐዋርያት ፩፥፫
💠በዓለ ዕርገት ለሐዋርያት የየሚላክላቸው አጽናኝ እንዲጠብቁ በኢየሩሳሌምም እንዲጠብቁ ያዘዘበት ነው።
“ከእነርሱም ጋር አብሮ ሳለ ከኢየሩሳሌም እንዳይወጡ አዘዛቸው፥ ነገር ግን፦ ከእኔ የሰማችሁትን አብ የሰጠውን የተስፋ ቃል ጠብቁ፤
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።” ሐዋ. ፩፥፬
💠ጌታችን ያረገው ደቀ መዛሙርቱን ከኢየሩሳሌም ወደ ቢታንያ አውጥቶ እያባረካቸው ነው።
“እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው።
ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ”። ሉቃ. ፳፬:፶
💠ጌታችን ወደ ሰማይ ያረገው ሐዋርያት እያዩት ከፍ ከፍ እያለ ነው።
“ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው።”
ሐዋርያት ፩፥፱
💠ጌታችን ዕርገት ዳግም እንደሚመጣም የተነገረበት ነው።
“እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤
ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደ ሰማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው”።
ሐዋ.፩፥፲
“በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።”
1ኛ ጢሞቴዎስ ፫፥፲፮
